ኢትዮጵያዊው የግብርና ባለሙያ  በኡጋንዳ  የFAO  ተወካይ ሆነው ተሾሙ

Date:

በምግብ ዋስትና እና በሥነ-ምህዳር መቋቋም ፕሮግራሞች ላይ ከአስር አመታት በላይ ልምድ ያካበቱት ኢትዮጵያዊው አቶ እዛና ካሳ፣ በኡጋንዳ የተባበሩት መንግስታት የምግብና እርሻ  ድርጅት (FAO) ተወካይ ሆነው ተሾሙ።

የኡጋንዳ መንግስት ይሁንታውን የሰጠበት ይህ ሹመት በድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ኩ ዶንግዩ የተከናወነ ሲሆን፣ አቶ እዛና አንቶኒዮ ኩዌሪዶን በመተካት ስራቸውን ይጀምራሉ።

ሹመቱ ድርጅቱ በአቶ እዛና ሰፊ የመስክ ልምድ እና በአፍሪካ ቀንድ ባሉ ውስብስብ አካባቢዎች በነበራቸው ውጤታማ የስራ አፈጻጸም ላይ ያለውን ጥልቅ እምነት የሚያሳይ መሆኑ ተገልጿል።

አቶ እዛና ካሳ ወደ ፋኦ የተቀላቀሉት እ.ኤ.አ. በ2015 በደቡብ ሱዳን የፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ በመሆን ሲሆን፣ ከዚያም በሶማሊያ የድንገተኛ አደጋ አስተባባሪና የከፍተኛ ፕሮግራም መኮንን በመሆን በሰብአዊ እርዳታና በልማት ስራዎች ላይ ስትራቴጂካዊ አመራር ሰጥተዋል።

ድርጅቱን ከመቀላቀላቸው በፊትም እንደ ‘አክሽን አፍሪካ ሄልፕ ኢንተርናሽናል’ ባሉ ታዋቂ አለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ በዳይሬክተርነት ደረጃ ሰርተዋል።

በትምህርት ዝግጅታቸውም ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በግብርና የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን፣ ከለንደን ዩኒቨርሲቲ በዘላቂ ግብርና እና ገጠር ልማት የማስተርስ ዲግሪያቸውን እንዲሁም ከዩናይትድ ስቴትስ ኢንተርናሽናል ዩኒቨርሲቲ (ናይሮቢ) የኤግዚኪዩቲቭ ኤምቢኤ አግኝተዋል።

አቶ እዛና በሹመታቸው ወቅት ባስተላለፉት መልእክት፣ “የአፍሪካ ዕንቁ” በመባል የምትታወቀው ኡጋንዳ በአካባቢው የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ያላትን እምቅ አቅም አድንቀዋል።

ከኡጋንዳ መንግስትና ከገጠር ማህበረሰቦች ጋር በመተባበር ዘላቂና ሁሉን አቀፍ የግብርና ስርዓትን ለመገንባት ቁርጠኛ መሆናቸውንም ገልጸዋል። ፋኦ ከኡጋንዳ ጋር ያለውን የቆየ አጋርነት በማጠናከር፣ በምርታማነት መጨመርና በገጠር ኢኮኖሚ ግንባታ ላይ ትኩረት አድርገው እንደሚሰሩም ይጠበቃል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...

ከ 50 ሚሊዮን በላይ መራጮች በማንዋልና በዲጂታል ተመዝግበዋል

ከየካቲት 28_መጋቢት 28 የመራጮች ምዝገባ ሲካሄድ እንደነበር ይታወቃል። በተለያዩ ጉዳዮች...