ኢትዮጵያ ባለፉት 6 ወራት ብቻ ከ704.4 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ ችላለች

Date:

ባለፉት ስድስት ወራት እንደሀገር በተከናወነ የተቀናጀ ሥራ ከ704 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ ተችሏል ።

የገቢዎች ሚንስቴር የ6 ወራት የገቢ አፈጻጸም ሪፖርት እንደሚያመላክተው ኢትዮጵያ በስድስት ወራት መሰብሰብ የቻለችው ከ704.4 ቢሊዮን ብር የሚልቅ ገቢ ባለፉት ጊዜያት ለዓመታት ሲሰበሰብ ከነበረው ገቢ የሚተካከል ነው ።

መንግሥት የሀገር ኢኮኖሚ ዕድገትን የሚደግፉ በርካታ የሪፎርም ስራዎችን እያከናወነ መሆኑ ለተገኘው ውጤት ቁልፍ መነሾ ነው።

አፈጻጸሙ በገቢዎች ሚኒስቴር በግማሽ ዓመቱ ለመሰብሰብ ከታቀደው 640 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ውስጥ 704 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ የዕቅዱን 110 በመቶ ማሳካት የተቻለበት ነው ።

የተሰበሰበው ገቢ ከባለፈው ዓመት ስድስት ወራት አፈፃፀም ጋር ሲነፃፀር የ63 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ብልጫ ያለው ሲሆን ይህም ኢትዮጵያ የውስጥ አቅሟን በማጎልበት እያንሰራራች ለመሆኑ ሁነኛ ማሳያ ተድርጎ የሚወሰድ ነው ።

በግማሽ ዓመቱ ከሀገር ውስጥ ታክስ 362 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር የተሰበሰበ ሲሆን ከውጪ ንግድ ቀረጥና ታክስ ከ341 ነጠብ 9 ቢሊዮን ብር በላይ ተስብስቧል ። ይህም ኢትዮጵያ በታሪኳ ከፍተኛውን የገቢ አፈጻጸም ያሳየችበት ሀገራዊ ስኬት ነው ።

የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢትዮጵያ እና የቻይና አየር መንገዶች የጋራ ስምምነት ተፈራረሙ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ቻይና ሳውዘርን አየር መንገድ በቻይና...

ሁቲዎች በሳዑዲ የነዳጅ ኩባንያ አስተዳደር ሕንጻ ላይ በፈጸሙት ጥቃት በእሳት ተያያዘ

የሳዑዲ አረቢያ የኢነርጂ ሚኒስቴር በአገሪቱ ምሥራቃዊ ግዛት የሚገኘው ከዓለም...

የሹመት ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)  ሹመት የሰጧቸው አመራሮች፡- 1. አቶ...

እንደዚህ ዓይነቱ ብልሹ ኣሰራርን ካላረምን በቀር መልካም ኣስተዳደርን …

በኣጠቃላይ በዚህ ዓመታዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኣጠቃላይ...