ሀገሪቱ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን ጨምሮ ከሌሎች ሀገራት ጋር በብሔራዊ ገንዘቦች ለመገበያየት ስምምነት ላይ መድረሷን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ አስታውሰዋል።
ይህም የኢትዮጵያን ጥቅም ባስጠበቀ መልኩ ንግድ እና ኢንቨስትመንትን እንደሚያሳልጥ ከኢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል። በተጨማሪም ውሳኔው፦
🔸 ኢትዮጵያ ከበርካታ ሀገራት ጋር የምታደርገውን የንግድ እና ኢንቨስትመንት ግኑኝነት እንደሚያጠናክር፣
🔸 የንግድ ሚዛን ለመጠበቅ እንደሚረዳ፣
🔸 በአንድ መገበያያ ላይ ጥገኛ መሆን የሚፈጥረውን አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚከላከል አንስተዋል።
#Sputnik
