ኢትዮ ቴሌኮም ለሚድያ አካላት በላከው እና ለደንበኞቹ በተለያዩ ማህበራዊ ገፆቹ ባሰራጨው መግለጫ በአሁኑ ወቅት ያለውን ማክሮ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ፣ የአገልግሎት ጥራትን በዘላቂነት ለማስጠበቅ የታሪፍ ማሻሻያ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ብሏል።
እናም የአገልግሎት ጥራትን በዘላቂነት ለማስጠበቅና የቴክኖሎጂ አቅሙን ለማሳደግ የሚያስችል ስትራቴጂካዊ የታሪፍ ማስተካከያ ይፋ አድርጓል።
በዚህም መሰረት ኢትዮ ቴሌኮም በአማካይ የ23% የዋጋ ጭማሪ ማድረጉን አስታውቋል።
ይህ ማስተካከያ የደንበኞችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንዲቻል ሶስት አበይት ነጥቦችን ማካተቱንም የጠቆመ ሲሆን፡፡ እነዚህም፦
- የቴሌብር ልዩ ስጦታ ማዕቀፍ፦ በቴሌብር በኩል ጥቅል ሲገዛ የነበረው የ10% ቅናሽ ወደ 20% ከፍ እንዲል ተደርጓል።
- ዋጋቸው ያልተቀየሩ ጥቅሎች፦ በርካታ ደንበኞች የሚጠቀሙባቸው 38 የተለያዩ ጥቅሎች ላይ ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ አልተደረገም።
- ዲጂታል አካታችነትን ለማስቀጠል፦ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚጠቀሙባቸው የ1 ብር፣ የ2 ብር፣ የ5 ብር እና የ1 ሰዓት ጥቅሎች ባሉበት እንዲቀጥሉ ተወስኗል።
ኢትዮ ቴሌኮም የዋጋ ጭማሪው ለኢትዮጵያውያን የዲጂታል አገልግሎት ተጠቃሚነት ቀጣይነት እንዲሁም የሀገሪቱን አካታች የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ የሚያፋጥን እንዲሆን በማሰብ ተመጣጣኝ እንዲሆን ማድረጉን ገልፃል፡፡
EthioTelecom
