እስራኤል እና ኢራን 4ኛ ቀን

Date:

እስራኤል እና ኢራን እያደረጉ ያሉት ጦርነት ዛሬ 4ኛ ቀኑን ሲይዝ ዛሬ በተሰሙ መረጃዎች ላይ ተከታዩን አጫጭር መረጃዎች አዘጋጅተናል

⚫ ጥቃቶች በእጅጉ እየተስፋፉ ቀጥለዋል። ኢራን በእስራኤል የነዳጅ ማጣሪያ እና የኃይል ማከፋፈያ ላይ ጥቃት ሰንዝራለች።

⚫ እስራኤል የዛሬው ጥቃት በምዕራብ ኢራን የሚገኝ ሆስፒታል ላይ ጥቃት ማድረሷ ሲገለጽ የኢራን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቃለ አቀባይ ጥቃቱን ተቃውመዋል።

⚫ ኢራን በእስራኤል የሚፈፀምባት ጥቃት እስካልቆመ ድረስ ከአሜሪካ ጋር በድርድሩ እንደማትሳተፍ ለኦማን እና ኳታር አስታውቃለች። ሁለቱ ሃገራት የአሜሪካ እና ኢራንን የኒውኪሊየር ድርድር ሲመሩ የነበሩ ሃገራት እንደሆኑ ይታወሳል።

⚫ የእስራኤል ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ያሂር ላፒድ አሜሪካ ከኢራን ጋር በሚደረገው ውጊያ እንድትሳተፍ ጠይቀዋል። መሪው፥ “ዶናልድ ትራምፕ ለዓለም ሰላም ሲሉ ተገቢውን እርምጃ ይወስዳሉ” ብለዋል።

⚫ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኔያሁ “የእስራኤል አየር ኃይል የቴህራንን ሰማይ ተቆጣጥሯል” ሲሉ ተናግረዋል። ኔታኔያሁ አክለውም” የቴህራን ዜጎች ለቀው እንዲወጡ ጠይቀናል፤ እርምጃ እንወስዳለን” ብለዋል።

⚫ ኢራን ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ 370 ሚሳኤሎችን ወደ እስራኤል ማስወንጨፏ ተሰምቷል። ኢራን በእስራኤል ጥቃቱ ከተከፈተባት ወዲህም የእስራኤልን የአየር መከላከል ጥሰው የገቡ ጥቃቶችን ፈፅማለች።

⚫ የእስራኤል ከፍተኛ ባለስልጣን እና አለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ የኢራን የኒውኪሊየር ማበልጊያን በተመለአተ የተለያዩ ሃሳቦችን አጋርተዋል። የእስራኤል ባለስልጣን በናታንዝ የኒውኪሊየር ማበልፀጊያ ከመሬት በታች ያለው ክፍል ጉዳት ደርሶበታል ሲሉ አለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ጉዳት አልደረሰበትም ብሏል።

⚫ እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃቱን ከጀመረች በኋላ 120 የኢራን የሚሳኤል ማስወንጨፊያዎችን መምታቷን እና ከጥቅም ውጪ ማድረጓን አስታውቃለች። እስራኤል ያወደመቻቸው የሚሳኤል ማስወንጨፊያዎች ኢራን ካላት ውስጥ 30 በመቶ ያህል ነው ብላች።

⚫ ኢራን በቴል አቪቭ በሰነዘረችው የሚሳኤል ጥቃት በቴል አቪቭ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ቅርንጫፍ መጠነኛ ጉዳት እንደደረሰበት አምባሳደሩ ገልፀዋል።

⚫ የእስራኤል ጦር በቴህራን ዲስትሪክት 3 የሚባለው እና ብዙ ኤምባሲዎች የሚገኙበት ቦታ የሚኖሩ ሰዎች ለቀው እንዲወጡ አስጠንቅቋል።  በአካባቢው የእስራኤል ጦር ምን አይነት ኢላማዎችን ለማጥቃት እንዳሰበ አልታወቀም።

⚫ ፓኪስታን ከኢራን ጋር የሚያዋስናትን ድንበር ዘግታለች። ፓኪስታን ላልተወሰነ ጊዜ ድንበሩ ተዘግቶ ይቆያል ብላለች።

⚫ በእስካሁኑ እስራኤል በኢራን በተፈፀመባት ጥቃት 24፤ ኢራን ደግሞ 224 ዜጎቻቸው በጦርነቱ ህይወታቸውን አጥተዋል።

Source: CNN, AL JAZEERA
Photo: Reuters, Mmiddle East Eye, AP

@TikvahethMagazine

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...