እንግሊዝ እና ኖርዌይ ወደ ሩብ ፍፃሜው ተቀላቀሉ

Date:

በአለም ዋንጫ ጥሎ ማለፍ ኖርዌይ ብራዚልን 2ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅላለች።

የኖርዌይን ወሳኝ የማሸነፊያ ግቦች ኤርሊንግ ሀላንድ 2x ማስቆጠር ችሏል።

የብራዚልን ግብ ኔይማር በፍጹም ቅጣት ምት አስቆጥሯል።

ኤርሊንግ ሀላንድ በአለም ዋንጫው 7️7ኛ ጎሉን ማስቆጠር ችሏል።

ብራዚል ከአስራ ስድስት ውስጥ ከአለም ዋንጫ ለመሰናበት ተገዳለች።

በሌላ በኩል እንግሊዝ አዘጋጇን ሜክሲኮን 3 ለ 2 በማሸነፍ ወደ ሩብ ፍፃሜው ተቀላቅላለች።በአስር ተጫዋች ሁለተኛውን አጋማሽ የተጫወቱት እንግሊዞች በሀሪ ኬን እና ቤሊንግሀም ሁለት ጎሎች አሸንፈው ወጥተዋል።

በጨዋታው ኳንሳህ በሰራው ጥፋት በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቶ ነበር። የሶስቱ አናብስት አምበል ሀሪ ኬን በውድድሩ ስድስተኛ ጎሉን ማስቆጠር ችሏል።

ሀሪ ኬን በአለም ዋንጫው በድምሩ ያስቆጠራቸውን የግብ መጠን ወደ 14 ከፍ አድርጓል።

ኖርዌይ በቀጣይ ዙር እንግሊዝን በሚያሚ ትገጥማለች።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጉምሩክ ኮሚሽን ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱን ገለጸ

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት 725.25 ቢሊዮን ብር...

ከ1.5 ሚሊዮን ዶላር የአፍሪካ ንፁህ ኢነርጂ ፈንድ አምስቱ አቅኚ የኢትዮጵያ ድርጅቶች ተመረጡ

በምስራቅ አፍሪካ የንፁህ ኢነርጂ አቅርቦትን በማሳደግ የስራ እድልን ለመፍጠርና...

ታላቅ የምስጋና እና የስጦታ መርሃ-ግብር ጥሪ!

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ባለፉት 5 ዓመታት ላበረከቱት ከፍተኛና ታላቅ...

የቀድሞዉ የኢራን ላዕላይ መሪ አያቶላሕ ዓሊ ኻምኔይ ተቀበሩ

ዩናይትድ ስቴትስና እስራኤል ባለፈዉ የካቲት ማብቂያ ላይ የገደሏቸዉ የኢራን...