ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን ከደረጃ በታች የሆኑ ምርቶች ተወገዲ

Date:

ይህንን ችግር ፈጥረዋል ያላቸውን ከ2,000 በላይ ድርጅቶች መቅጣቱንም ሰምተናል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ይህንን ያለው በዛሬው እለት የላቀ ውጤት አስመዝግበዋል ያላቸውን ሰራተኞቹን በሸለመበት እንዲሁም ለአገልግሎት አመቺ እንዲሆን በሚል ለሰራተኞቹ ያዘጋጀውን የደምብ ልብስ ባስተዋወቀበት ወቅት ነው፡፡

ለማህበረሰቡ የሚቀርበውን ምግብና መድሃኒት ደህንነቱን የሚቆጣጠረው ባለስልጣኑ ባለፈው የ2017 የበጀት ዓመት በአጠቃላይ በአቀማመጥ በአመራረትና በሽያጭ ወቅት በምግብና መጠጦች ጥራትና ደህንነት ላይ የጥራት ጉድለት ፈጥረዋል ባላቸው ከ2 ሺህ 49 በላይ ድርጅቶች ላይ ከገንዘብ ቅጣት ለህግ እስከ ማቅረብ የደረሰ እርምጃ መውሰዱን ተናግሯል፡፡

በዚህም ከእነዚህ ድርጅቶች የተሰበሰቡ 200 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ ምግብ ነክ ምርቶች መወገዳቸውን የነገሩን የአዲስ አበባ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሙሉእመቤት ታደሰ ናቸው፡፡

በተለይ የምግብ ምርቶች ከደረጃ በታች ሆነው ሲገኙ ስማቸውንና አይነታቸውን በመዘርዘር፤ እነዚህ ምርቶች ከደረጃ በታች ናቸውና አትጠቀሟቸው የሚሉ ማስጠንቀቂያዎች ከባለስልጣኑ ተደጋግሞ የሚሰማ መሆኑን ተከትሎ ከማስጠንቀቅ ይልቅ ችግር የተገኘባቸውን ምርቶች ከገበያው ለምን አትሰበስቡም? ያልናቸው ዋና ስራ አስኪያጇ፤ ይህንን ማዘዝ ያለበት የፌድራሉ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን ነው፤ በባለስልጣኑ ከገበያ እንድንሰበስብ ስንታዘዝ የተባሉትን ምርቶች ከገበያ እንሰበስባለን ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል የከተማዋ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን የመድሃኒት ምርቶች ላይ ባደረገው ቁጥጥር ተመሳሳይ የእርምት እርምጃ የተወሰደባቸው ከ300 በላይ የመድሃኒት ማቅረብና ሽያጭ ላይ የተሰማሩ የመድሃኒት መደብሮችና ሌሎችም ድርጅቶች ናቸው ብለዋል ወ/ሮ ሙሉእመቤት፡፡

የቁጥጥር ስራውን ለማበርታት እንዲሁም ወደ ቁጥጥር ስራ ሲሰማሩ የሰራተኞቹን ማንነት በቀላሉ መለየት እንዲቻል ከ1080 ለሚበልጡ ሰራተኞቹ የደምብ ልብስ ማዘጋጀቱንና የተናገረው ባለስልጣኑ ከዚህ በኋላ ሰራተኞቹ ያለ ደምብ ልብስ እንደማይሰሩ እወቁት ብሏል፡፡

ሸገር 102.1

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኮሪያ ዘማቾች ያስመዘገቡት አኩሪ ታሪክ በዓለም ሲታወስ ይኖራል

75ኛ ዓመት የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ በዓል አዲስ አበባ በሚገኘው...

አሜሪካ በጣለችው የባህር ላይ እገዳ ሳቢያ ኢራን 4.8 ቢሊዮን ዶላር አጣች

በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ በኦማን ባህረ ሰላጤ ላይ...

ኢሕአፓ ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ማራዘሙን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሚያዚያ 30 ቀን 2018...

እሁድ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ

መነሻውንና መድረሻውን መስቀል አደባባይ የሚያደረገው ዓለም አቀፉ የዛይድ የበጎ...