ካይሮ በዓባይ ውሃ በሌላ አዲስ ግንባታ መጣች

Date:

ይህ የግብፅ አዲስ የበረሃ ከተማ ፕሮጀክት ሀገሪቱ ከአባይ/ናይል ወንዝ ውሃ ከምታገኘው አመታዊ ኮታዋ ከ 7 በመቶ በላይ ፍጆታ እንዳለው የአረቡ አለም ሚዲያዎች ዘግበውታል። መጠኑም 4 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትርመሆኑ ነው።
  የግብርና ምርቷም ሆነ አጠቃላይ ኢኮኖሚዋ በውሃ እጥረት ሳቢያ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰበት ስትል የቆየችው ካይሮ፣ በዛሬው ዕለተ እሁድ ይፋ ያደረገችው ይህ የበረሃ ከተማ ከመዲናዋ ካይሮ 42 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በስተ ምዕራብ አቅጣጫ ከምትገኘዋ ጂሪያን ከተማ አቅራቢያ ነው የሚገነባው።
ለከተማዋ የሚቀርበው የዓባይ ወንዝ ውሃን በመጥለፍ በመስታወት በሚሰሩ መተላለፊያ ቤቶች የሚጓጓዝ ሲሆን በዬቀኑ 11 ሚሊዮን ኪዩቢክ ያህል የዓባይ ውሃ ነው እንዲደርስ የታቀደው።
   የበረሃ ከተማ  ፕሮጀክቱ አዲስ የእርሻ ልማት ጭምር አካትቶ የሚገነባ ሲሆን ይህም 2.28 ሚሊዮን ኤከር የሚሰፋ እርሻ የሚጀመርበት ነው።

በግብፅ ቀደም ሲል የተጀመረውና እየተጠናቀቀ የሚገኘው የሁለተኛው ካይሮ አዲስ የከተማ ግንባታዋ ካሁኑ ፕሮጀክት እጅግ የበለጠ ውሃ ከናይል ዓባይ የሚቀርብለት መሆኑ የሚታወቅ ነው። ዛሬ ደግሞ በሌላ የከተማ ፕሮጀክት ሌላ ከፍተኛ የውሃ አቅርቦት ከዓባይ ወንዝ እንዲቀርብ አቅዳ ተነስታለች።

  #የዓባይልጅ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...