ኬንያ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ስትራቴጂ ይፋ አደረገች

Date:

ከአውሮፓዊያኑ 2025-2030 ተግባራዊ የሚደረገው ስትራቴጂ፤ በኤ.አይ አስተዳደር፣ በፈጠራና ክህሎት ዘርፎች ኬንያን ግንባር ቀደም ለማድረግ ያለመ ነው።

በተጨማሪም ሀገሪቷ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥነ-ምህዳር ውስጥ በአፍሪካ ብሎም በዓለማቀፍ ደረጃ ወሳኝ ሚና እንድትጫወት ስትራቴጂው አጋዥ ነዉ ተብሏል።

ስትራቴጂው በሀገሪቱ ብሔራዊ የኤ.አይ የስራ ቡድንና አስተባባሪ ኮሚቴ ከመንግሥት ተቋማት፣ ከግሉ ዘርፍ፣ ከአካዳሚክ፣ ከሲቪል ማህበረሰብና ከዓለማቀፍ አጋሮች ጋር ሰፊ ምክክር በማድረግ መዘጋጀቱ ተጠቁሟል፡፡

ይህ ስትራቴጂ ከአፍሪካ ህብረት የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ ጋር የሚጣጣም መሆኑንም ቴክ አፍሪካ ኒውስ አስነብቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት በዛሬ ዕትሟ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ነሔሴ 16 2018 ዓ.ም ገበያ...

ቱርክ ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ አወጣች

ቱርክ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ ዓለም አቀፍ...

በመቀለ የሚካሄደው የአሸንዳ በዓል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተሰረዘ

በትግራይ በርካታ ታዳሚ በሚገኝበት በየዓመቱ የሚከበረው የአሸንዳ ባህላዊ በዓል...

የኢትዮጵያ ፖስታ 3 ሺሕ የሚጠጉ ቅርንጫፎቹን ወደ ባንክ ኤጀንትነት ለመቀየር እንቅስቃሴ ጀመረ

የኢትዮጵያ ፖስታ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ 3 ሺሕ በሚጠጉ ቅርንጫፎቹ...