ወጋገን ከሁለት ዓለማቀፍ ባንኮች ጋር ስምምነት መፈጸሙ ተገለጸ

Date:

የ85 ሚ. ዶላር የዓለም አቀፍ ንግድ ፋይናንስ ዋስትና አግኝቷል

ወጋገን ባንክ ከአፍሪካ ቀጠናዊ የኢንቨስትመንትና የልማት ፋይናንስ ቡድን (TDB) እና የአፍሪካ ኢምፖርት ኤክስፖርት ባንክ ጋር በፈፀመው ስምምነት በድምሩ የ85 ሚሊዮን ዶላር የዓለም አቀፍ ንግድ ፋይናንስ ዋስትና ማግኘቱን ይፋ አደረገ፡፡

የተፈፀመው ስምምነት ወጋገን ባንክ ከዓለም አቀፍ ባንኮች ጋር ያለውን ስትራቴጂክ አጋርነት በማጠናከር በዓለም አቀፍ ንግድ ግብይት ዙሪያ ለሚያቀርበው የሌተር ኦፍ ክሬዲት እንዲሁም ከገቢና ከወጪ ንግድ ጋር ለተያያዙ ሰነዶች ዋስትና የመስጠት አቅሙን በማጠናከር ለበርካታ ደንበኞች አገልግሎቱን ተደራሽ ማድረግ የሚያስችለው ይሆናል፡፡

በተጨማሪም በወጋገን ባንክና በተጠቀሱት ባንኮች መካከል የተፈፀመው የፋይናንስ ዋስትና ስምምነት፣ ባንኩ ለረጅም ዓመታት ከበርካታ ዓለም አቀፍ ባንኮች ጋር በመስራት ያካበተው በጠንካራ መተማመን ላይ የተመሰረት የስራ ግንኙነት መገለጫ ሲሆን፤ በቀጣይም ከሌሎች ዓለም አቀፍ ባንኮች ጋር ተመሳሳይ የስራ ግንኙነት የመመስረት እድል የሚፈጥርለት እንደሚሆን የካፒታል ዘገባ አስነብቧል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...