የልብስ ስፌት አገልግሎት ሰጪዎች የኤክሳይዝ ታክስ አንዲከፍሉ ተወሰነ

Date:

የገቢዎች ሚኒስቴር በልብስ ስፌት አገልግሎት ላይ የሚጣለውን የኤክሳይዝ ታክስ አከፋፈል በተመለከተ አዲስ ማብራሪያ ሰጥቷል።

ሚኒስቴሩ፣ የልብስ ስፌት ፋብሪካዎች “የአገልግሎት ሰጪ ነን” በሚል ምክንያት ከኤክሳይዝ ታክስ ነፃ መሆን እንደማይችሉ ባወጣው ሰርኩላር ደብዳቤ ላይ አመልክቷልተ

ከዚህ ቀደም የገንዘብ ሚኒስቴር በሰጠው ማብራሪያ፣ አምራቾች ከደንበኞች የሚቀርብላቸውን ጨርቅ የመስፋት አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅት የኤክሳይዝ ታክስ እንዲከፍሉ አይጠየቁም ተብሎ የነበረ ቢሆንም፣ ይህ አሰራር የታክስ ገቢ እንዲታጣ ምክንያት መሆኑ ተገልጿል።

በመሆኑም በኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ቁጥር 1186/2012 (እንደተሻሻለው) መሠረት፣ በHS Code 50.07 እስከ 63.04 የተመደቡ የጨርቃ ጨርቅና የተሰፉ ልብሶች ምርቶች የኤክሳይዝ ታክስ የሚጣልባቸው በመሆኑ፣ የልብስ ስፌት ፋብሪካዎች ግዴታቸውን እንዲወጡ መታዘዙን ካፒታል ጋዜጣ ለመረዳት ችሏል።

የገንዘብ ሚኒስቴር በቁጥር ታ/ክ/4/5/952 በቀን 01/04/2018 በሰጠው አዲስ ማብራሪያ መሠረት፦ የኢንቨስትመንትና የንግድ ፈቃድ ያላቸው የልብስ ስፌት ፋብሪካዎች ለኤክሳይዝ ታክስ ዓላማ የመመዝገብ ግዴታ አለባቸው።

በተጨማሪም “የልብስ ስፌት አገልግሎት ሰጪ ነን” በሚል ሰበብ ከታክስ ነፃ መሆን አይችሉም የተባለ ሲሆን አምራች ፋብሪካዎችና የሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች ይህንን አውቀው ተገቢውን ክትትል እንዲያደርጉ የገንዘብ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

በታህሳስ 7 ቀን 2018 ዓ.ም በገቢዎች ሚኒስትር የተላለፈዉ ይህ ውሳኔ በዘርፉ ሊሰበሰብ የሚገባውን የታክስ ገቢ በአግባቡ ለመሰብሰብና አሰራሩን ግልፅ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ10 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ጥቅምት 12 ቀን 2019...

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ የፕላቲንየም ብራንድ የማስተር ካርድ ይፋ አደረጉ

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ደንበኞች የፕሪሚየም...

የአሜሪካ የደህንነት ኃላፊ ኢራንን አስጠነቀቁ

ቡሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተር ጄይ ክላይተን አርብ ዕለት ኢራን በውጭ...

ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ  በአመት ከ1.1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ታጣለች

85 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በግብርናው ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን...