በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ሀብቴ ዱላ (ዶ/ር) እንደተናገሩት የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አዲሱ የቡታጅራ ካምፓስ በቀጣዩ ዓመት ተማሪዎችን መቀበል ይጀምራል።
የቡታጅራው ካምፓስ የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስተር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በአካባቢው ማህበረሰብ በቀረበላቸው ጥያቄ መሠረት እንዲሠራ ቃል ገብተው እንደነበር የሚታወስ ነው ፡፡
በቀድሞ ጠቅላይ ሚንስተር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ቃል የተገባው የቡታጅራ ካምፓስ ከአመታት በኋላ ከ2018 ዓ.ም ጀምሮ መደበኛ ተማሪዎች ተቀብሎ ትምህርት ለማስጀመር ቅድመ ሁኔታዎች መጠኛቀቃቸውን ኢፕድ ዘግቧል ፡፡
