በሱዳን ዛምዛም ካምፕ ግድያ፣ አስገድዶ መደፈር እና እገታ መበራከቱን ባለስልጣናት አስታወቁ

Date:

በሰሜን ዳርፉር በሚገኘው ዛምዛም የተፈናቀሉ ሰዎች ካምፕ ውስጥ የግድያ፣ የአስገድዶ መድፈር እና የመሰወር ድርጊቶች መበራከቱ ተገልፆል። በሰሜን ዳርፉር ግዛት ከኤል ፋሸር በስተደቡብ 12 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው የዛምዛም ካምፕ አስተዳደር በካምፑ ውስጥ በፈጣን የድጋፍ ሰጪ ሃይሎች የሚደርሰውን በደል ለመከታተል የሚያስችል መድረክ ከፍቷል።የዛምዛም ካምፕ አስተዳደር ቃል አቀባይ ሞሃመድ ካሚስ ዱዳ ለሱዳን ትሪቡን እንደተናገሩት ከሆነም ባለፈው ሳምንት በድረ-ገጽ ላይ የወጣው የቅርብ ጊዜ መረጃ 31 የአስገድዶ መድፈር ጉዳዮችን፣ 52 በግዳጅ የተሰወሩ እና 173 የተገደሉ ሰዎች ስለመኖራቸው ያሳያል።

ነገር ግን በመድረኩ ላይ የሚጠቀሙና መረጃ የሚያቀርቡ አካላት በኤል ፋሸር እና በአቅራቢያው በታዊላ የሚገኙና አብዛኞቹም የተፈናቀሉ በመሆናቸው የኢንተርኔት አገልግሎት የማያገኙ ቢያገኙም ለመጠቀም ገንዘቡ የሌላቸው በመሆኑ ምክንያት መድረኩ በርካታ ፈተናዎች እንዳሉበት ጠቁመዋል።በተጨማሪም በካምፑ ላይ በተፈፀመው ጥቃት ወይም በተፈናቀሉበት ወቅት በርካታ ነዋሪዎች ስልኮቻቸውን እንደጠፉ እና በርካቶች ወደ ደህና አካባቢዎች ለሚያደርጉት ጉዞ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ስልኮቻቸውን ለመሸጥ መገደዳቸውን እና የደረሰባቸውን በደል በሰነዶቻቸው ላይ ተጽዕኖ እንዳሳደረ ተነግሯል። አርኤስኤፍ ዛምዛም ካምፕን ከወራት ድብደባ በኋላ በሚያዝያ 11 ከሶስት ቀናት ግጭት በኋላ ተቆጣጥሯታል። ጥቃቱ የእርዳታ ሰራተኞችን ጨምሮ 400 ንፁሀን ዜጎች የገደለ ሲሆን 406ሺ ሰዎች እንዲሰደዱ ያደረገ 180 ሺዎቹ ደግሞ በካምፑ ውስጥ እንደታሰሩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገልጿል።

መሀመድ ካሚስ ዱዳ በሱዳን ጦር እና በአርኤስኤፍ መካከል የእርስ በርስ ግጨቱ ቢቀጥልም በኤል ፋሸር የነበረው ሁኔታ መረጋጋቱን ዘግቧል። በጤና ጣቢያዎች እና ሆስፒታሎች ከፍተኛ የመድሃኒት እጥረት እና የምግብ ዋጋ መናር መከሰቱን ተከትሎ በኤል ፋሸር በሰላማዊ ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለውን ስቃይ አፅንኦት ሊሰጥበት ይገባልም ተብሏል።በአሁኑ ሰዓት በሱዳን ላይ ያለው የዋጋ ንረት ስንመለከት አንድ የልብስ ማጠቢያ ሳሙና 6,000 የሱዳን ፓውንድ፣ አንድ ኪሎ ሥጋ 12ሺ ፓውንድ በጥሬ ገንዘብ በባንክ ከሆነ ደግሞ 20ሺ ፓውንድ ይሸጣል ተብሏል። አንድ በርሜል ውሃ በጥሬ ገንዘብ 8,000 ፓውንድ ያስወጣል፣ በባንክ ዝውውር ከሆነ ደግሞ ወደ 12,000 ፓወንድ ከፍ ይላል። ኤል ፋሸር በከፍተኛ የገንዘብ እጥረት እየተሰቃየች ሲሆን ይህም ዜጎች 100ሺ ፓውንድ በባንክ ካላቸውና በጥሬ ገንዘብ መቀየር ከፈለጉ የሚያገኙት 65,000 ፓወንድ ብቻ ነው።

ከተማዋ ከአንድ አመት በላይ በአርኤስኤፍ ሃይሎች ጥብቅ ከበባ ውስጥ ስትሆን ነዳጅን ጨምሮ በርካታ እቃዎች ወድመዋል ወይም ተዘርፈዋል። ይህም የአካባቢው ነዋሪዎች “ቃሮ” በመባል የሚታወቁትን የአህያ ጋሪዎችን በመጠቀም በጥይት የተጎዱትን ወደ ጤና ጣቢያዎች እንዲያጓጉዙ አስገድዷቸዋል።

ዳጉ_ጆርናል

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...