“የበርበሬ ዐውሎ ነፋስ” በድምቀት ተመረቀ

Date:

በደራሲ አበረ ሽፈራው የተፃፈው “የበርበሬ ዐውሎ ነፋስ” የተሰኝው አዲስ መፅሐፍ ዋልያ መጽሐፍት አዳራሽ በርካታ ታዳሚያን በተገኙበት በድምቀት ተመረቀ ::


በዚህ የመጽሐፍ ምርቃት ፕሮግራም ላይ ሰለሞን ሳህለ፣ ቢንያም ውብሸት ፣ ኤደን ሃብታሙ ፣ እናኑ ግርማ ፣ ህይወት እምሻው ከመጽሐፉ ላይ በንባብ እቅቅርበዋል:: ደራሲ አበረ ሽፈራው በአዲስ ልሳን ጋዜጣ እና በፉና በጋዜጠኝነት አገልግሏል::

የእለቱ የክብር እንግዳ በመሆን መጽሐፉን በይፋ የመረቁት የመጽሐፉ ደራሲ አበረ ሽፈራው ወላጅ አባት እና የአበረ የትዳር አጋር የሆነችው የደራሲ ህይውት እምሻው እናት ነበሩ:: የደራሲው ወላጅ አባት በምርቃት ፕሮግራሙ ላይ እንደተናገሩት :-

” ከልጅነቱ ጀምሮ መጽሐፍ ማንበብብ ይወድ ስለነበር እኔም በወር እስከ ሶስት መጵሐፍትን እየገዛሁ እንዲያነብ አደርግ ነበር::
ዛሬ እርሱም መጽሐፍ ጽፎ የእርሱን መጽሐፍ ለመመረቅ ስለበቃሁ በጣም ደስ ብሎኛል::


እንክዋ ደስ ያለህ ” በማለት ደስታቸውን ገልጸዋል::ደራሲውም ለአባቱ የአክብሮትና የምስጋና ሥጦታ አበርክቷል::

(ይትባረክ ዋለልኝ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...