የትግራይ ህክምና ማሕበር፣ ለጤና ባለሙያዎችጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ ጠየቀ

Date:

የትግራይ ህክምና ማሕበር፣ ለጤና ባለሙያዎች የደሞዝና ጥቅማጥቅሞች ጥያቄ መንግሥት አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ ጠየቀ።

ማሕበሩ  ግንቦት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ለጤና ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ፣ መንግሥት ለጤና ባለሙያዎች ጥያቄና መብት ተገቢውን ትኩረትና ምላሽ ከመስጠት ይልቅ፣ በአንዳንድ የአገሪቱ አካባቢዎች የጤና ባለሙያዎችን ጥያቄ እየጣሰ ተገቢ ያልሆነ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን አስታውቋል።

እነዚህ የሞያ አጋሮቻችን እንዲፈቱ አስፈላጊው  ጫና እንዲደረግ  ለጤና ሚኒስቴር ያሳሰበው ማሕበሩ፤ ሁሉም የሞያ ማህበራትና የጤና ባለሞያዎች ለችግሮቹ  መፍትሄ ለማበጀት ግልፅና ሁሉን ያሳተፈ ውይይት እንዲደረግም ጠይቋል።

በተመሳሳይ የኦሮሚያ የጤና ባለሙያዎች ማኅበር ትላንት ባወጣው መግለጫ፣ በመላ አገሪቱ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ያነሱትን የመብት ጥያቄ እንደሚደግፍ አስታውቆ፣ መንግሥት ለጥያቄያቸው ምላሽ እንዲሰጥ መጠየቁ ይታወሳል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ደቡብ ሱዳን የነዳጅ ቅድመ-ክፍያ ውሎችን እንዳትፈጽም አገደ

የለንደን ፍርድ ቤት ደቡብ ሱዳን ከአሁን በኋላ አዳዲስ የነዳጅ...

” ከ140 በላይ ጠጠር አምራች ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ ቆመዋል ” – ማህበሩ

" ካላቸው ቅሬታ ማቅረብ ይችላሉ። ግን መሬቱ መቼ እንደተወሰደባቸው...

ትራምፕ “በኢራን ላይ ሊፈጸም ታቅዶ የነበረውን ጥቃት አንፈጽምም” አሉ

ትራምፕ በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ ቁልፍ የአሜሪካ አጋር ሀገራት መሪዎች...

በነዳጅ ጭማሪ በኬንያ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ የአራት ሰዎች ሕይወት አለፈ

በኬንያ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን ተከትሎ በዋና ከተማዋ ናይሮቢ በጸጥታ...