የአማራ ባንክ  አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ  31.5 ቢሊዮን ብር ደረሰ

Date:

የአማራ ባንክ 2024/25 በጀት አመት ስራ አፈጻጸም ጉባኤ ላይ የባንኩ ወና ስራ አስፈጻሚ ዮሐንስ አያሌው (ዶ/ር) በሪፖርታቸው ይፋ  እንዳደረጉት የባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ ብር 31.5 ቢሊዮን ማድረስ መቻሉ እና የደንበኞቹን ቁጥር ከ2.4 ሚሊዮን በላይ እንዲሁም የቅርንጫፎቹን ቁጥር 316 ማድረስ ተችሏል፡፡

  ባንኩ በቅርቡ ባስተዋወቀው ለወዳጄ የዲጂታል አነስተኛ ብድር አገልግሎቱ ከ1.6 ቢሊዮን ብር በላይ ከ97 ሺህ በላይ ለሆኑ ደንበኞች ብድር ያቀረበ ሲሆን፤ ከዚህ ውስጥም ሴቶች፣ የአካል ጉዳተኞችና በአነስተኛ ንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች ዋነኞቹ ተጠቃሚ እንደሆኑ  ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ ባንኩ 70.8 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የውጪ ምንዛሬ ማግኘት እንደቻለ ገልጸዋል፡፡ የባንኩ አጠቃላይ ካፒታል 8.6 ቢሊዮን ብር ማድረስ እንደተቻለም አስታውቀዋል፡፡

በብድር አሰባሰብ ረገድ በዓመቱ 10.4 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ የተቻለ ሲሆን፣ ይህም ከባለፈው ተመሳሳይ በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ236.3 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፡፡

አማራ ባንክ የሰጠው ጠቅላላ የብድር መጠን ከብር 26 ቢሊዮን በላይ ማድረሱንና የተበላሸ የብድር መጠኑ ብሔራዊ ባንክ ካስቀመጠው ከፍተኛ ጣራ በታች መሆኑን የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ዮሐንስ ገልጸዋል፡፡

KGEthiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...