
ሆስፒታሉ በፋርማሲ መስጫ አገልግሎት የመድሃኒት የመገኘት ምጣኔውን 80 በመቶ ያህል ተደራሽ ማድረግ መቻሉን ገልፆል።
ሆኖም የመድኃኒት አቅርቦት ችግርን አስመልክቶ አሁን ላይ የሳይካትሪ መድሀኒቶች በተለያዩ ምክንያቶች መቅረብ አለመቻላቸዉን አስታዉቋል።
የመሰረታዊ መድሀኒት ÷ የህይወት አድን መድሃኒት እንዲሁም የትሬሰር መድሃኒት አቅርቦት ላይ ጥሩ አፈፃፀም ማሳየቱን አስታዉቋል።
ሆስፒታሉ የመድሃኒት አቅርቦት በተመለከተ በዋናነት መድሃኒት ገዝቶ የሚያቀርበው ከኢትዮጵያ የመድሃኒት አቅርቦት አገልግሎትና ከግል የመድሃነት አቅርቦት ድርጅቶች ነዉ።
የአማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በፎረንሲክ ሳይካትሪ የወንጀልና የፍትሐብሔር ተመርማሪ ለ413 ሰዎች አገልግሎት መስጠት መቻሉን አስታዉቋል።
ከዚህ በተጨማሪ የላብቶሪ አገልግሎትን በ2017 በጀት ዓመት በሆስፒታሉ ውስጥ የሚሰጡ የላብራቶሪ የምርመራ ዓይነቶችን በቁጥር 85 ለማድረስ አቅዶ በመጀመሪያ 6 ወራት ውስጥ 72 የምርመራ ዓይነቶችን ለተገልጋዮቹ ተደራሽ ማድረግ ችያለሁ ብሏል፡፡
ሆስፒታሉ የህክምና አገልግሎት መስጫ ቦታ እጥረትና የማስፋፊያ ስራዎች በበቂ ደረጃ አለመከናወናቸው የተገልጋይ እርካታ ለማምጣት የመሰረተ-ልማት ችግር ዋነኛ ማነቆ ሆነው መቀጠላቸውን አንስቷል፡፡
ethio f.m 107.8