የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፣ እናት ፓርቲ፣ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)፣ አንድ ኢትዮጵያ ዲሞከራሲያዊ ፓርቲ እና አማራ ዮናዊ ንቅናቄ በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን ቅንጅት መሠረቱ፡፡
ላለፉት ተከታታይ ዓመታት በትብብር በጋራ ሲሰሩ የነበሩት የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፣ እናት ፓርቲ፣ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)፣ አንድ ኢትዮጵያ ዲሞከራሲያዊ ፓርቲ እና አማራ ግዮናዊ ንቅናቄ ትብብራቸውን ሕጋዊ ቅርጽ በማስያዝ ቅንጅት መሥርተዋል።
