የአብርሆት ቤተ መጻሕፍት ትልቅ የዕውቀት ማዕከል ሆኖ እያገለገለ ይገኛል

Date:

የአብርሆት ቤተ መጻሕፍት ትልቅ የዕውቀት ማዕከል ሆኖ እያገለገለ ይገኛል አሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤና የአብርሆት ቤተ መጻሕፍት የቦርድ ሰብሳቢ ቡዜና አልከድር እና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት የአብርሆት ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት አሰጣጡን የሚያጎለብቱ የዲጂታል ሲስተሞችን አስጀምሯል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚህ ወቅት÷ የአብርሆት ቤተ መጻሕፍት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጭነት ተገንብቶ ለአገልግሎት መብቃቱን አስታውሰዋል።

ቤተ መጻሕፍቱ አገልግሎት መስጠት በጀመረ ማግስት በመዲናዋ ትልቅ የዕውቀት ማዕከል ሆኖ እያገለገለ እንደሚገኝ ገልጸው÷ በዕውቀትና ክህሎት የተካነ ትውልድ በማፍራት ለኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ መሰረት የሚጥል ስፍራ መሆኑንም አብራርተዋል።

አገልግሎት አሰጣጡን በአዳዲስ አሰራሮች በማላቅ ዕውቀትን ለሚሹ ሁሉ የንባብ ባህልን በማዳበር የዕውቀት ሽግግር ድልድይ በመሆን አገልግሎት እየሰጠ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የአብርሆት ቤተ መጻሕፍት የዲጂታል ሥርዓቶችም የንባብ አገልግሎት አሰጣጥ በተሻለ ጥራትና አቅም የሚያልቁ መሆናቸውን አመላክተዋል።

የዲጂታል አገልግሎቶቹም የቤተ መጻሕፍቱን የተቀናጀ አስተዳደር በማሳለጥ ተመራማሪዎች የጥናትና ምርምር ስራዎቻቸውን ካሉበት ቦታ ሆነው በቀላሉ ማከናወን የሚያስችሉ ናቸው ብለዋል።

በቀጣይም ዜጎች የአብርሆት ቤተ መጻሕፍትን በ24 ሰዓት አገልግሎት የፈጠረውን ምቹ የንባብ ምኅዳር ሊጠቀሙበት እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የአብርሆት ቤተ መጻሕፍት ዋና ዳይሬክተር ሙሉቀን ታሪኩ በበኩላቸው÷ ቤተ መጻሕፍቱ የዜጎችን የንባብ ፍላጎት በሚመጥን መልኩ የ24 ሰዓት አገልግሎት እየሰጠ እንደሆነ መናገራቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

በዛሬው ዕለት የተጀመሩት የዲጂታል ሲስተሞች የአብርሆት ቤተመጻሕፍት በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ አቅም የሚፈጥሩ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ አዲስ አበባ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ...

የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የ5 በመቶ የአደጋ ሥጋት ምላሽ ፈንድ ክፍያን ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱት ሁለቱም የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ማለትም ኢትዮ ቴሌኮም እና...

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዚዳንት ለኢራን ህዝብ – “እኛ ከእናንተ ጋር ነን”

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት ሮቤርታ ሜትሶላ፥ የኢራን መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ...

አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ሊኖራት ይገባል

በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ቋሚ ውክልና...