የኢቢኤስ ቴሌቪዥን መስራችና ስራ አስኪያጅ አማን ፍስሃፅዮን ባሳለፍነው ሳምንት ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለዩ ይታወሳል።
የአስከሬን አቀባበል የክብር ስንብት እና የቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴው የስንብት ስነ-ስርዓቱን እንደሚከተለው አዘጋጅቷል።
የስንብት መርሃግብሩ የሚካሄደው የፊታችን ሐሙስ የካቲት 12/ 2018 ዓ.ም በአድዋ ሙዚየም ነው።
ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጉዞ ከመኖሪያ ቤታቸው ወደ አድዋ ሙዚየም ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ለስንብት መርሃግብር ስርዓት አስከሬኑ አደዋ ሙዚየም ይደርሳል።
ከቀኑ 8፡00 ሰዓት አስከሬኑ ወደ መጨረሻ ማሪፊያው ጉዞ ይጀምራል። ከቀኑ 9፡00 ሰዓት በጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር የግብዓተ መሬት ስነ-ስርዓት ይፈጸማል።
