የአንድ ቀዶ ጥገና ሐኪም አሳዛኝ ህይወት በትግራይ….

Date:

እኔ በትግራይ ውስጥ በአንድ አጠቃላይ ሆስፒታል የምሰራ የቀዶ ጥገና ሐኪም ነኝ።

ለሕዝቤ በቅንንነት ለማገልገል የገባሁት መሐላ ከባድ የሆኑ እና አስጨናቂ የሥራ ሁኔታዎችን በቀንና በሌሊት እንዲሁም በቀጣይ ቀናት እንድሰራ አስገድደውኛል።

በመጋቢት ወር ብቻ 56 ቀዶ ህክምናዎችን አጠገቤ ረዳት ሳይኖረኝ ለብቻዬ አከከናውኛለው!
በእነዚህ ግዚያት አንድ Scrub ነርስ፣ አንድ Runner Nurse፣ እና አንድ የአንስቴዥያ ነርስ ብቻ ነበሩ። የአንስቴዥያ ቡድናችን ሁለት ነርሶችን ያካተተ ሲሆን አንዱ በወርሃዊ የሥራ እረፍት የሚገኝ ሲሆን።
በአጠቃላይ ያለን የነርስ ሠራተኞች ብዛት 11 ብቻ ነው።

እነዚህ ቀዶ ህክምናዎች እንደሚመለከተው ናቸው!

13 ከበድ ያሉ በቀጠሮ ሚሰሩ ቀዶ ህክምናዎች (Elective)

3 የታይሮይድ ቀዶ ህክምና (Thyroidectomies)

3 ሀሞት ጠጠር (Cholecystectomies)

2 የፕሮስቴት ቀዶ ህክምና (Transvesical Prostatectomies)

2 የትልቁ አንጀት ክፍል ቀዶ ህክምና (Sigmoidectomies)

2 PPV ligations

1 Ileostomy Reversal

16 ድንገተኛ የሆኑ ቀዶ ህክምናዎች (Emergency)

የትርፍ አንጀት ቀዶ ህክምና (Appendectomies)

Exploratory laparotomies with appendectomy, bowel derotation, and Hartmann’s colostomy

22 አነስ ያሉ ፕሮሲጀሮች

  • ‎15 Abscess drainages (breast, hand, perianal, submandibular)
  • ‎4 Corrective circumcisions for AUR (post-traditional phimosis)
    ‎1 Tube thoracostomy
    thoracostomy)

5 አነስተኛ የቀጠሮ ቀዶ ሕክምናዎች (Elective)

በእነዚህ ሁሉ ውስጥ
290 ተመላላሽ የቀዶ ህክምና ታማሚዎችን
74 ውስጥ ተኝተው ሚታከሙ የቀዶ ህክምና ታማሚዎችን ተመልከቻለሁ።

በዚህ ከባድ የሥራ ጫናና በበዛበት ሁኔታ ውስጥ፣ ኑሮ እሳት በሆነበት ጊዜ.. ወርሃዊ ደመወዝዬ 12,760 ብር (በአሁኑ እለታዊ ምንዛሬ 96 ዶላር) ብቻ ነው።

ይህ የአብዛኛው ኢትዮጵያ ያሉ የጤና ባለሞያዎች ታሪክ ነው። ከፍተኛ የስራ ጫና ውስጥ ያለን፣ በዝቅተኛ ደመወዝ ምንሰቃይ ፣ ትኩረት እና ክብር የተነፈግን!

ለህዝቡ ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆንን ተረስቷል!

ከትግራይ ክልል ብቻ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ከ115 በላይ ዶክተሮች የተሻለ ህይወት ፍለጋ ይህን ሀገር ጥለው ተሰደዋል።

እኛ ድሎት እና ሀብት አልጠይቅንም፤
ክብር! እውቅናና ከሰው እኩል መታየትን እንጂ!

ዶክተር ተክላይ ሰሎሞን – የቀዶጥገና ሐኪም

Hakim

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ፤ አደረሰን

ሰማያት ተከፈቱ ፣ ምስጢርም ተገለጠ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዘመዷ ቅድስት...

አባቴ ለእኔ አባት ብቻ አልነበረም፤ ለእናቴ ታማኝ ባል፣ ለሁላችንም ደግሞ የደስታ ምንጭ ነበር

"አባዬ… ዛሬ ላለሁበት ማንነት መሰረት የሆንከኝ አንተ ነህ!" ​የአርቲስት...

የአንበሶቹ ትንሳኤ፦ የዳካር እንባ እና የቴራንጋ ድል

​በዳካር ሰማይ ስር ዛሬ ጨረቃ አልወጣችም፤ ይልቁንም በሚሊዮን የሚቆጠሩ...

የጥምቀት በዓል በመላ ሀገሪቱ በድምቀት እየተከበረ ነው

የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እና በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት...