የአዲስ አበባ ከተማ ቤተ መፅሐፍቶች ለ810 ሺህ አንባቢ አገልግሎት ሰጥተዋል

Date:

በተያዘው 2018 ግማሽ ዓመት ለ 810 ሺህ አንባቢያን የከተማዋ ቤተመፅሐፍቶች አገልግሎት መስጠታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ባህልና ኪነጥበብ ቢሮ ገልጿል።

አሁን ላይ ባለው የመፅሐፍት ዋጋ ንረትና የብር የመግዛት አቅም መዳከም የተነሳ አንድን መፅሐፍ እስከ 67 ሺህ ብር ድረስ ቢሮው እገዛ ነው ሲሉ በቢሮው የቤተ መፅሐፍት ዳይሬክተር ዶ/ር አዲሱ መኮንን ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ባህልና ኪነጥበብ ቢሮ ከዓመታዊ በጀቱ ከፍተኛውን በጀት ለመፅሐፍት ግዢ እንደሚያውልም ገልጸዋል።

በከተማዋ 82 የሕዝብ ቤተመፅሐፍቶች መኖራቸውን ገልፀው ተጨማሪ ደረጃቸውን የጠበቁ መፅሐፍት ቤቶችን ለማስገንባት በጀት ተመድቦ ስራዎች ተጀምረዋል ብለዋል።

ከአዲስ አበባ ባለፈ ነዋሪዎች በሚበዙባቸው የሸገር ከተማ አካባቢዎች ቤተ መጽሐፍቶችን ለማስፋፋት ጥናቶች እየተደረጉ መሆናቸውን ሰምተናል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ አዲስ አበባ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ...

የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የ5 በመቶ የአደጋ ሥጋት ምላሽ ፈንድ ክፍያን ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱት ሁለቱም የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ማለትም ኢትዮ ቴሌኮም እና...

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዚዳንት ለኢራን ህዝብ – “እኛ ከእናንተ ጋር ነን”

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት ሮቤርታ ሜትሶላ፥ የኢራን መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ...

አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ሊኖራት ይገባል

በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ቋሚ ውክልና...