የአፍሪካ ህብረት አዲሱ የአሜሪካ ታሪፎች የአስርተ አመታት የንግድ ትብብርን አደጋ ላይ ይጥላሉ አለ

Date:

የአፍሪካ ህብረት እንዳስታወቀው በአህጉሪቱ ላይ በአሜሪካ የተጣሉ አዲሶቹ ታሪፎች የአስርተ አመታት የዘለቀውን “በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ የንግድ እና የትብብር” ግንኙነትን አደጋ ላይ እንደሚጥሉ አስጠንቅቋል።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ማሃሙድ አሊ የሱፍ የአሜሪካ መንግስት በወሰደው የጣሪፍ ጭማሪ ላይ ያላቸውን ጥልቅ ስጋት በመግለጽ ይህንንም ውሳኔ እንደገና እንዲያጤነው አሳስበዋል።

አሜሪካ የረዥም ጊዜ እሴቶች እና በጋራ ምኞቶች ላይ የተመሰረተውን የረጅም ጊዜ አጋርነት ከማጠናከር ይልቅ ማዳከም ተገቢ አይደለም ማለታቸው ተነግሯል።

በተለይም እንደ ትልቅ የጨርቃ ጨርቅ ላኪ የሆነችው ሌሶቶ እስከ 50 በመቶ የሚደርስ ታሪፍ የተጣለባት ሲሆን ደቡብ አፍሪካ፣ ማዳጋስካር እና ቦትስዋና ደግሞ ከ 30 በመቶ በላይ በሆነ የታሪፍ ጭማሪ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን የመከላከያ ስምምነቶችና የፖለቲካዊ ድጋፎች

በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ የመጣውን የጸጥታ ስጋት ተከትሎ፣ ጣሊያን ለባህረ...

የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ”ንዋይ” የተሰኘ መተግበሪያን ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ዜጎች...

የነዳጅ እጥረት አሽከርካሪዎችን ለከፋ እንግልት እየዳረገ ነው

በአዲስ አበባ እና በልዩ ልዩ የክልል ከተሞች የሚስተዋለው የነዳጅ...

ሼክ ኢብራሂም ቱፋ በኢራን ኤምባሲ በመገኘት ሀዘናቸውን ገለጹ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼክ ኢብራሂም...