የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የሁሉ ብድር አብረው ለመስራት ስምምነት ተፈራረሙ

Date:



ስምምነቱ የሁሉ ብድር እና ቁጠባ አባላት ማንኛውም የፋይናንስ አገልግሎት በባንኩ የዲጂታል ባንከ ቻነሎች በመጠቀም በቀላሉ አገልግሎቱን ማግኝት እንዲችሉ የሚረዳ ነው።

የኢ.ን.ባ የመርቻንት ኤንድ ኤጀንት ማኔጅመንት ዳይሬክተር አቶ ብሌን ኃይለሚካኤል በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት ይህ ስምምነት የዲጂታል ባንክ አገልግሎትን ተጠቃሚዎችን ቁጥር ከማሳደግ ባለፈ አካታችነትን እውን በማድረግ የማህበሩ አባላት የሲቢኢን ዲጂታል ባንክ አማራጮችን በመጠቀም ግዜና ጉልበታቸው ቆጥበው ለመገልገል የሚረዳቸው ነው ብለዋል።

የሁሉ የብድር እና ቁጠባ ህብረት ስራ ማህበርም ከሁለት አመት በፊት የተቛቛመ እና ከ22 ሺህ በላይ ደምበኞች ያሉት ሲሆን እስካሁን ከ 1.3 ቢልየን በላይ ብድር ሰጥቷል ።


በመሆኑም ለነዚህ ደምበኞቹ የሚሰጠው ብድር እና መደበኛ ቁጠባን በቀላሉ ለመሰብሰብ እነዚህ የሲቢኢ የዲጂታል ባንክ አማራጮች አይነተኛ ሚና እንደሚጫወቱ የሁሉ ብድር እና ቁጠባ ህ/ስ/ማ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ መሳፍንት ደበበ ገልፀዋል።

ይህም ወጪን ከመቀነስ፣የፋይናንስ አካታችነት ከማረጋገጥ፣ የዲጂታል ክፍያዎችን ከፍ ከማድረግ እና የደምበኞች እርካታን ከመጨመር አኳያ ፋይዳው የጎላመሆኑ በዚሁ ጊዜ ተገልጿል።

የኢ.ን.ባ እስካሁን ከተለያዩ የመንግስት እና የግል ተቛማት ጋር መሰል ስምምነቶች መፈራረሙ የሚታወስ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከባለፈው  ዓመት የ130 በመቶ ብልጫ  አተረፈ

መጋቢት 30 በተጠናቀቀው የኩባንያው በጀት ዓመት 15.9 ቢሊዮን ብር...

በዕውቀቱ በታላቁ ዓለም አቀፍ ፌስቲቫል ላይ ተመረጠ

ዝነኛው ደራሲና ገጣሚ በዕውቀቱ ሥዩም በስፔን ባርሴሎና በሚካሄደው 41ኛው...

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 1 2018 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

በኢትዮጵያ ነፃ ኘሬስ ከ25 ዓመት በላይአገልግለናል !!! -የአርበኞች አደራና የትውልዱ...

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...