የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ22 ኤርፖርቶች መሪ እቅድ እንደሌላቸው ሪፖርት አሳየ

Date:



በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የኤርፖርት መሰረተ ልማት ስራዎች እና ኤሮኖቲካል ያልሆኑ ገቢዎች አፈጻጸም ውጤታማነትን በተመለከተ በተሰራ ኦዲት 22 ኤርፖርቶች መሪ እቅድ ወይንም (Master Plan) እንደሌላቸው የኦዲተር መስሪያቤት ሪፖርት ጠቅሷል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የሚያስተዳድራቸው ኤርፖርቶች መሪ ዕቅድ (Master Plan)፣የመሬት አጠቃቀም ካርታ እና የይዞታ ካርታ ሊኖራቸው ይገባ ነበር ያለው ሪፖርቱ ነገር ግን ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት በቀር የተቀሩት 22 ኤርፖርቶች የሌላቸውም ሲል አስረድቷል፡፡

ከተጠቀሱት ስምንት ኤርፖርቶች የመሬት አጠቃቀም ካርታ (Land Use Plan) የተዘጋጀላቸው ሲሆን፤ የተቀሩት 15 ኤርፖርቶች የመሬት አጠቃቀም ካርታ አልተዘጋጀላቸውም ብሏል መስሪያቤቱ ፡፡

ይይዞታ ካርታ የሌላቸው ሶስት አየር ማረፊያዎች እንዳሉ እና የይዞታ ማረጋገጫ ካርታቸው ትክክለኛ ቦታውን አወሳኝ በሚያሳይ መልኩ ያልተሰራላቸው አራት የአየር ማረፊያዎች አሉ ተብሏል፡፡

በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት፣ በድሬደዋ እና በአሶሳ በኤርፖርቶቹ ዙሪያ የሚገኝ እስከ 13 ኪ.ሜ ስፋትያለው የመሬት አጠቃቀም ለአዕዋፋት መስህብ የተጋለጠ መሆኑን እና ይህም ለበረራ ስጋት የሚፈጥር እንደሆነ ዛሬ ለፓርላማ የቀረበው ባለ 65 ገጽ የኦዲተር መስሪያቤት ሪፖርት ጠቅሷል፡፡

የአሶሳ ኤርፖርት ግንባታ ቀድሞ የአዋጭነት ጥናት ባለመሰራቱ ኤርፖርቱ ከዋናው መንገድ አጠገብ በመሆኑ ተንቀሳቃሽ ነገሮች ለበረራ ስጋት መፍጠራቸውም በግኝት ተረጋግጧል፡፡

በተመሳሳይ የጎንደር አፄ ቴዎድሮስ ኤርፖርት የአየር መንግዱ ክልል አጥር ባለመታጠሩ እና ክፍት በመሆኑ እንስሳት እና ያልተፈቀደላቸው ሰዎች በቅጥር ግቢው እንደሚገቡ ተጠቅሷል፡፡

ሸገር 102.1

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመረጃ ነጻነት አዋጅን በሙሉ ድምፅ አጸደቀ

በምክር ቤቱ የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ እውነቱ...

በቬንዝዌላ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ የ32 ሰዎች ህይወት አልፏል

በቬንዙዌላ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን 7.2 እና 7.5...

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ “ሉሲ” ላገኟት ፕሮፌሰር የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጠ

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ፥...

የሳህለወርቅ ዘውዴ አዲሱ አለም አቀፍ ሹመት በተመድ ልዩ ተልእኮ ተሰጣቸው

የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ በተመድ ዋና ፀሀፊ...