የኢትዮጵያ የቀይ ባህር ጉዞ ከግማሽ መንገድ በላይ ተራምዷል 

Date:

የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ በዲጂታል ኢቢሲ ምረቃ ስነስርአት ላይ ባስተላለፉት መልእክት ኢትዮጵያ በሁለንተናዊ የልማት ስራ ስኬት በማስመዝገብ ላይ ትገኛለች ብለዋል።

ኢትዮጵያ በከተሞች በኮሪደር ልማት አዲስ ምዕራፍ ከፍታለች ያሉት ሚኒስትሩ ላለፉት ሰባት አመታት አለም አቀፋዊ ተፅእኖ መቋቋም የሚችል ኢኮኖሚ መገንባቱን ገልጸዋል ።

በማህበራዊ ዘርፍም የሰለጠነ የሰው ሀይል  እና በበጎነት መርህ መልካም ዜጋ በማፍራት ረገድ ሰፊ ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል ። በሜጋ ፕሮጀክቶች ረገድ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምርቃት ከቀናት በኋላ እንደሚከናወን ጠቁመዋል ።

ዶ/ር ለገሰ የባህር በር ተጠቃሚነትን በሚመለከትም የኢትዮጵያ የቀይ ባህር ጉዞ ከግማሽ መንገድ በላይ መራመዱን አስታውቀዋል ።

ኢትዮጵያ በሁሉም እንቅስቃሴዎች እያገኘች ያለውን ጉልህ ስፍራ ለማስተጓጐል  ታሪካዊ ጠላቶቻችን ከሚዘውሯቸው የውስጥ ባንዳዎች ጋር በመተባበር ከፍተኛ የፕሮፓጋንዳ ፈተና ተከፍቷል ብለዋል።

የኢትዮጵያን ገፅታ ለማጠልሸት የሚደረገውን እንቅስቃሴ  የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን በዲጂታል ምህዳር በመተባበር የመመከት ስራ እንደሚጠበቅባቸው ሚኒስትሩ አመላክተዋል ።

ዶ/ር ለገሰ ግጭት እና ብጥብጥን የኢትዮጵያ ማዳከሚያ ስልት አድርገው የሚጠቀሙ ሀይሎችን አላማ በመረዳት ዜጎችም የሚጠበቅባቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል ።

በቤተልሔም ገረመው

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ምንገድ ላይ

(በእውቀቱ ስዩም) በቀደም ከሆነ ቦታ ተነስቼ ወደ አልሆነ ቦታ ስራመድ...

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ በጡረታ ከኃላፊነታቸው ተሰናበቱ

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያንና የአዲስ አበባ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ...

አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ አዲስ መግለጫ አወጣች

ታዋቂዋ አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ ለስፖርት ወዳጆችና ለደጋፊዎቿ ወቅታዊ መረጃ...