የደቡብ አፍሪካ መሪ ራማፎሳ ወደ አሜሪካ አቀኑ፤ ነገ ከትራምፕ ጋር ይገናኛሉ

Date:

የፕሬዝዳቱ ፅህፈት ቤት “የጉብኝቱ ዓላማ በአሜሪካና በደቡብ አፍሪካ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ዳግም ማስተካከል እና ማነቃቃት ነው” ብሏል።

ጉብኝቱ በዋናነት የሁለትዮሽ፣ የኢኮኖሚ እና የንግድ ግንኙነቶችን እንደገና ማነፅ ላይ ያተኩራል።

አሜሪካ በአፍሪካነሮች (ነጭ ደቡብ አፍሪካውያን) ላይ ያነጣጠሩ የመሬት ወረራዎች ዙሪያ ባቀረበችው ክስ ምክንያት በአሜሪካ እና በደቡብ አፍሪካ መካከል ያለው ግንኙነት ተበላሽቷል። ትራምፕ “በዘር ላይ የተመሰረተ መድልዎ” ሰለባዎች ናቸው በማለት የአፍሪካነር “ስደተኞችን” አሜሪካ ውስጥ ለማስፈር በየካቲት ወር ትዕዛዝ ሰጥተዋል። ባለፈው ሰኞ የመጀመሪያው ቡድን አሜሪካ ደርሷል።

ፕሪቶሪያ ክሱን መሠረተ ቢስ እና ፖለቲካዊ ያለችው ሲሆን ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ምንም ዓይነት የዘር መድልዎ የለም ብላ ተከራክራለች።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...