Home ዜና የጀርመን ቻንስለር አሜሪካ የጣለችውን ታሪፍ ተቃወሙ

የጀርመን ቻንስለር አሜሪካ የጣለችውን ታሪፍ ተቃወሙ

የጀርመን ቻንስለር አሜሪካ የጣለችውን ታሪፍ ተቃወሙ

  • ከአውሮፓ ጠንካራና አግባብ ያለው ምላሽ ይሰጣል ብለዋል

አሜሪካ በጀርመን ላይ የጣለችውን ታሪፍ ‹‹መሰረታዊ ስህተት ነው›› ያሉት ቻንስለር ኦላፍ ሾልዝ፤ በጉዳዩ ላይ ከአሜሪካ መንግስት ጋር ለመነጋገር ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡ ይሁንና ከአሜሪካ ጋር የሚደረገው ድርድር የማይሳካ ከሆነ፣ ጠንካራና አግባብ ያለው መልስ ከአውሮፓ እንደሚሰጥ ገልፀዋል፡፡

የጀርመን ኢኮኖሚ ሚኒስትር ሮበርት ሀቤክ በበኩላቸው፤ የአውሮፓ ህብረት በሚሰጠው ምላሽ የአሜሪካ አንጋፋ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች እንደሚጎዱ አስረድተዋል፡፡ ‹‹ትልልቅ የቴክኖሎጂ ድርጅቶቹ በአውሮፓ ውስጥ የሚያስደንቅ የገበያ የበላይነት ያላቸው ናቸው፤ ምክንያቱም እኛ ከታክስ ነፃ ስላደረግናቸው ነው›› ብለዋል፡፡

ሚኒስትሩ እንደገለፁት፤ የአውሮፓ ህብረት የሚሰጠው የአፀፋ ምላሽ የኦንላይን አገልግሎት ሰጪዎች ላይ የሚያተኩር ይሆናል፡፡ ፕሬዚደንት ትራምፕ ትላንት ባወጡት አለም አቀፍ ታሪፍ፤ ‹‹የነፃነት ቀን›› ማለታቸውን የጠቀሱት የጀርመኑ ሚኒስትር፤ ይሁንና ይህ ውሳኔ ለአሜሪካ ሸማቾች የነፃነት ሳይሆን የዋጋ ግሽበት ቀን ነው ብለዋል፡፡

ጀርመን ወደ አሜሪካ ከኬሚካሎች እስከ መኪና በማስገባት ከአውሮፓ አገራት ቀዳሚ ናት፡፡ ይሁንና ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ በሆነው አዲሱ ታሪፍ መሰረት ከጀርመን ወደ አሜሪካ የሚገቡ ምርቶች የ25 ፐርሰንት ታክስ ይጣልባቸዋል፡፡ ጀርመን ለአሜሪካ በብዛት ከምታቀርባው ምርቶች መካከል ቮልስዋገን፣ መርሰዲስና ቢኤምደብሊው አውቶሞቢሎች በቀዳሚነት ተጠቃሽ ናቸው፡