የገንዘብ ሚኒስቴር እ.ኤ.አ በ2025 የመጨረሻ ሩብ ዓመት የሚካሄደውን ጠንካራ የግምጃ ቤት ሰነዶች (T-Bills) የጨረታ መርሃ ግብር ይፋ ማድረጉን አስታውቋል።
ከመስከረም 21 እስከ ታኅሣሥ 15 ቀን 2018 ዓ.ም. የሚካሄደው ይህ የሶስት ወራት መርሃ ግብር በአጠቃላይ 243.05 ቢሊዮን ብር የሚገመት የዕዳ ሰነድ ለሀገር ውስጥ ባለሀብቶች የሚያቀርብ ሲሆን። መንግሥት የሀገር ውስጥ የዕዳ ገበያን ለማጥለቅና ግልጽነትን ለማሳደግ በያዘው ቀጣይነት ባለው የፋይናንስ ማሻሻያ አጀንዳ ውስጥ ቁልፍ እርምጃ መሆኑ ተመላክቷል።
በተለይም ይህ የዕዳ ሰነድ አቅርቦት በየሁለት ሳምንቱ የሚካሄድ ሲሆን፣ ለባንኮች፣ ለኢንሹራንስ ኩባንያዎች፣ ለጡረታ ፈንድ እና ለሌሎች ተቋማት የተረጋጋ የኢንቨስትመንት ዕድልን ይፈጥራል።
ባለሀብቶች በአራት የተለያዩ የጊዜ ገደቦች ማለትም 28 ቀናት፣ 91 ቀናት፣ 182 ቀናትና 364 ቀናት ላይ መጫረት የሚችሉ ሲሆን፣ ይህም የኢንቨስትመንት ፖርትፎሊዮአቸውን በተለያየ መልኩ እንዲያስተዳድሩ ያስችላቸዋል።
CapitalNews
