Home ልዩ ልዩ ዜና የጌዲዮን ሙላቱ ስርዓት ቀብር ተፈፀመ

የጌዲዮን ሙላቱ ስርዓት ቀብር ተፈፀመ

የጌዲዮን ሙላቱ ስርዓት ቀብር ተፈፀመ


በመቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ቀደምት ተገልጋይ የነበረው የጌዲዮን ሙላቱ ስርዓት ቀብር መቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ፊት ለፊት በሚገኘው አያት መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል።

በስርዓት ቀብሩ ላይ የመቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል መስራች እና ዋና ሥራ አስኪያጅ ቢኒያም በለጠን ጨምሮ የማዕከሉ አረጋውያን አንዲሁም ወደጆቹ ተገኝተዋል።

ጌዲዮን በትልልቅ ሆስፒታሎች የልብ ሕክምና ሲደረግለት የነበረ ሲሆን፤ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በድንገተኛ ሕክምና ክፍል ተኝቶ ልዩ ክትትል እየተደረገለት በትናትናው ዕለት ሚያዝያ 4 ቀን 2017 ዓ.ም በሕክምና ላይ እያለ በ37 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ለመላ  የመቄዶንያ  ቤተሰቦች  ወዳጆቹ  መፅናናትን እንመኛለን 
ነብስህን  በአፀደ ገነት  ፈጣሪ ያኑር ።