‎የፋርማሲዎች የርቀት ገደብ መመሪያ

Date:

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ፋርማሲዎች አንዱ ከሌላው ቢያንስ በ100 ሜትር ርቀት ላይ እንዲገኙ የሚደነግገው አዲሱ መመሪያ፣ በዘርፉ ሰፊ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኗል።

የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ይህንን መመሪያ ተግባራዊ ያደረገው ፋርማሲዎች በአንድ አካባቢ ብቻ ተከማችተው እንዳይቀሩና በሌሎች አካባቢዎች የሚስተዋለውን የመድኃኒት እጥረት በመቅረፍ ተደራሽነትን ለማስፋት እንደሆነ ገልጿል።

‎የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ወይዘሮ ወርቅነሽ ብርቄ እንደተናገሩት፣ ቁጥጥሩ አዲስ ፈቃድ በሚያወጡት ላይ ብቻ ሳይሆን መመሪያውን ባልተገበሩ ነባር ተቋማት ላይም ጭምር ተፈጻሚ ይደረጋል። በአንጻሩ የኢትዮጵያ የፋርማሲ ማኅበር በመመሪያው ላይ ያለውን ቅሬታ እያሰማ ይገኛል።

‎የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዳንኤል ዋቅቶሌ፣ አሰራሩ በተለያዩ ምክንያቶች ሥራ አቁመው ወደ ተግባር ለመመለስ የሚፈልጉ አንጋፋ ባለሙያዎችን የመስሪያ ቦታ ሊያሳጣ እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸዋል። እንደ ፕሬዚዳንቱ ማብራሪያ፣ የመደብሮች የውድድር መለኪያ መሆን ያለበት ከርቀት ይልቅ በመድኃኒት ጥራትና ብዛት ላይ ነው፤ በመሆኑም ነባር ባለሙያዎችን ከገበያ ሊያስወጣ የሚችለው ይህ መመሪያ በድጋሚ ሊፈተሽ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

‎ባለስልጣኑ በበኩሉ በርቀቱ ገደብ ምክንያት የተገኙ ለውጦችን በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግና ከባለሀብቶች ጋር ውይይት እንደሚያካሂድ አስታውቋል። ማንኛውም የፋርማሲ አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም ፈቃድ ካገኘ በኋላም ቢሆን፣ ጥብቅ የጥራትና የአገልግሎት አሰጣጥ ቁጥጥር እንደሚደረግበት ተገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...

ከ 50 ሚሊዮን በላይ መራጮች በማንዋልና በዲጂታል ተመዝግበዋል

ከየካቲት 28_መጋቢት 28 የመራጮች ምዝገባ ሲካሄድ እንደነበር ይታወቃል። በተለያዩ ጉዳዮች...

በኦሮሚያ ክልል የ4.5 ሚሊዮን ዶላር የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ

ፈያ ኢንተግሬትድ ዴቬሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን በኦሮሚያ ክልል የሚከሰቱ የበሽታ ወረርሽኞችን...