ቢሳን ኦውዳ የተባለችው ፍሊስጤማዊቷ ጋዜጠኛ የእስራኤል ወታደሮች የምግብ እና የውሃ አቅርቦትን በማቋረጣቸው እና ከአካባቢዉ ለቀዉ እንዲወጡ ትዕዛዝ በማውጣታቸው ምክንያት በጋዛ ያለው ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መቋቋም የማይቻልበት ደረጃ ላይ ደርሷል ብላለች።
ኦውዳ ለአልጀዚራ እንደተናገረችው ከሆነም “ለሁለት ሳምንታት ገደማ በቀን አንዴ ብቻ ምግብ እየተመገብኩ ነው፣ ምክንያቱም እስራኤል ለ77 ቀናት ምንም አይነት ምግብ ወደ ጋዛ እንዳይገባ ከልክላለችና” ስትል ተደምጣለች።ጋዜጠኛዋ አክላም “እስቲ አስበው ዶክተሮች፣ ነርሶች፣ የሲቪል መከላከያዎች፣ ሁሉም የድንገተኛ አደጋ ምላሽ ሰራተኞች፣ ሁሉም ከዚህ ጋር እየተፋለሙ ነው እየኖሩ ያሉት” ስትልም ተናግራለች።
ምንም እንኳ አሁን ላይ የእስራኤል መንግስት ወደ ጋዛ የተገደበ ሰብአዊ እርዳታ እንዲገባ ቢፈቅድም የአሜሪካ እስላማዊ ግንኙነት ምክር ቤት (CAIR) ግን የእስራኤል መንግስት ዘጠኝ የእርዳታ መኪኖች ብቻ ወደ ጋዛ እንዲገቡ መፍቀዱን ተቀባይነት የሌለው ሲል አውግዟል።“የተገደበው የእርዳታ አቅርቦት” “በጋዛ ውስጥ ለተከበቡት ሁለት ሚሊዮን ፍልስጤማውያን ወንዶች ፣ ሴቶች እና ሕፃናት የረሃብ ስጋትን ለማስወገድ ምንም አያደርግም” ሲል ምክር ቤቱ በመግለጫው አስታውቋል።
“ይህ ሙሉ በሙሉ በቂ ያልሆነ የስነ-አእምሮ ትንታኔ በኔታንያሁ የዘር ማጥፋት መንግስታዊ ስልት ጋዛን ለመያዝ እና ለማጥፋት ቆርጦ የተነሳ እና ከዚያም የተረፉትን ፍልስጤማውያንን ለማባረር የሚያደርገው ጥረት አካል ነው” ሲልም አክሏል።
