በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር በአብማ ክፍለከተማ ቀበሌ 01 ልዩ ቦታው ዩንቨርሲቲ እንግዳ መቀበያ ህንፃ ግንባታ ፊትለፊት ከሚገኘው አካባቢ የወንጀል ድርጊቱ ተፈፅሟል።
በአካባቢው የሻይ ቤት ባለቤት የሆነችውን ሸዋዬ አለኸኝ የተባለችውን ግለሰብ የፍቅር ጓደኝነት በማቅረብ አብረን እንኑር በማለት ጥያቄ ያቀርብላታል።
በነጋታው ተከሳሹ ባልታወቀ ምክንያት አንገቷን ጠምዝዞ በማነቅ በመግደሉ የአካባቢው ማህበረሰብ ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠቱ ፖሊስ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር በማዋል አስፈላጊው የምርመራ ስራ በማጣራት መዝገቡን ለሚመለከተው የፍትህ አካል መላኩን የ1ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ የታክቲክ ወንጀል መርማሪ ሳጅን አበበ ገልጸዋል ።
የምስራቅ ጎጃም ዞን አቃቢ ህግ ከፖሊስ የደረሰውን የምርመራ መዝገብ በማደራጀት እና በማስረጃ በማጠናከር ክስ መስረቶ መዝገቡን ለምስራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማስተላለፍ መቻሉን መርማሪው መናገራቸውን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል ።
የምስራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት ተከሳሽ ቢንያም ፈንታ ትዕዛዙ ጥፋተኛ መሆኑ በሰው እና በህክምና ማስረጃ በመረጋገጡ በ8 አመት ፅኑ እስራት መቀጣቱን ተገልጿል ።ከተፈጸመው የወንጀል ድርጊት አኳያ አቃቢ ህግ የቅጣት ይግባኝ መጠየቁን እና ተከሳሹ ከዚህ በፊት በ2012 ዓ.ም በማታለል እና በማጭበርበር ወንጀል ተከሶ በሌለበት 1አመት ከ5 ወር ተቀጦ ፖሊስ ሲያፈላልገው እንደነበረ ብስራት ሬዲዮ ከደብረ ማርቆስ ከተማ ፖሊስ ያገኘው መረጃ ያመላክታል።
