ዲያስፓራ አዳባባይ መገናኛ አካባቢ የደረሰ አደጋ

Date:


ዲያስፓራ አዳባባይ መገናኛ አካባቢ በደረሰዉ የተሽከርካሪ አደጋ ምክንያት አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገድ እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳሰበ፡፡


በአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የየካ ክፍለ ከተማ የትራፊክ ዲቪዥን ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ጋሻ ሁነኝ ሙሉጌታ እንደተናገሩት አደጋዉ 10፡30 አካባቢ በዲያስፓራ አዳባባይ በታክሲ ተርሚናሉ አካባቢ የደረሰ ሲሆን በአደጋዉ ሁለት ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዉ በህክምና ላይ ይገኛሉ፡፡


በታክሲ ተርሚናሉ ዉስጥ በተለምዶ ቅጥቅጥ የሚባለዉ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ወደ ኋላ ሲያሽከረክር ወድቆ ተንጠልጥሎ እንደሚገኝ ጨምረዉ ገልጸዋል፡፡


ተሽከርካሪዉ በአሁኑ ወቅት ከላይኛዉ ትሚናል ወደ ታችኛዉ ተርሚናል ተንጠልጥሎ ይገኛል፡፡


የእሳትና አደጋ መከላከል አሽከርካሪዎች በቦታዉ ደርሰዉ ተሽከርካሪዉን ለማንሳት ጥረት እያደረጉ መሆኑን የገለጹት ሃላፊዉ ተጨማሪ አደጋ እንዳይከሰት ክትትል እየተደረገ ይገኛል፡፡


ከቀበና መጥተዉ ወደ ኮተቤ የሚሄዱ ተሽከርካሪዎች በሚናሮል ጀርባ በኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ባለዉ አማራጭ መንገድ እንዲጠቀሙ አሳስበዋል፡፡


የትራፊክ ፖሊሶች በአካባቢዉ የትራፊክ እንቅስቃሴዉን በማሳላጥ ላይ እንደሚገኙም የየካ ክፍለ ከተማ የትራፊክ ዲቪዥን ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ጋሻ ሁነኝ ሙሉጌታ ተናግረዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...