ዶ/ር ፍትህ ወልደሰንበት በታጩበት የአፍሪካን ቢውልደርስ እና አፍሪካን ኢምፖክት በሁለቱም የደብል ኦስካር ተሸላሚ ሆኑ

Date:


ለአምስተኛ ጊዜ በተዘጋጀው የኢተዠንተርናሽናል አፍሪካን ቢውልደርስ ኮንፍረንስ ኮትዲቯር አቢጃን ላይ ቅዳሜ በ29/03/2025 እ.ኤ.አ በተካሄደው ፕሮግራም ነው የሴንትራል ያማረች ሀዋሳ ሆቴል የኢትዮጵያ ሆቴል እና ቱሪዝም አሰሪዎች ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት እንዲሁም የኢትዮጵያ እና የምስራቅ አፍሪካ እጅ ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት የሆኑትን ዶ/ር ፍትህ ወልደሰንበትን በሁለቱም ዘርፍ ተሸላሚ አድርጓቸዋል።

በፕሮግራሙ ላይ መቀመጫቸውን በአቢጄን ያደረጉ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት አምባሳደሮች፣ በምዕራብ አፍሪካ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት የማህበር መሪዎች እና በተለያዩ ዘርፍ ዕጩ የነበሩ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ተገኝተውበታል።

በኮንፍረንሱ የተገኙ በኮትዲቫር እና በካሜሮን ባለሙሉ ስልጣን የኢትዮጵያ አምባሳደር ክብርት ሽታዬ ምናለ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ለአፍሪካ አንድነት ሰላም እና ዕድገት በአድዋ ኮሎናይዜሽንን የመከተች ቀዳሚ ሀገር መሆኗን ገልፀው አዘጋጆቹንም ለዚህ አፍሪካዊ ሽልማት ኢትዮጵያን በመምረጣቹ እናመሠግናለን ብለዋል።

በፕሮግራሙ ንግግር ያደረጉት ተሸላሚው ዶ/ር ፍትህ ወልደሰንበት የስኬታቸው መሠረቱ በቅርቡ በሞት ያጣናቸውን የሴንትራል ያማረች ሀዋሳ ሆቴል መስራች የወ/ሮ አማረች ዘለቀ ጥንካሬ፣ ስትራቴጂካዊ የስራ እና የገበያ አመራር ልዩ እና የማይዋዥቅ ለህብረተሰብ ተኮር የሆን “መስጠት መቀበል” ነው የሚል መርሆችና እና የሀገራችን ምቹ የስራ ሁኔታ ነው ያሉ ሲሆን የሀገራችን ኢትዩጵያ በአለም ልዩ የሚያደርጋትን የምድረ ቀደምት; የቡና መገኛ; የራስ ቋንቋ ፊደላትና ቁጥር; እጅግ ብዙ የቱሪስት መዳረሻዎችን; ብርቅዬ እና የአፍሪካ ኩራት የሆነ አየር መንገዳችን ያሉትንና እና ሌሎችንም በተገቢው ለተሳታፊዎች ገልፀዋል። ተሳታፊዎችንም በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ; ጉብኝት እንዲያደርጉ ጋብዘዋል።

በዝግጁቱም የሚዲያ ተፅዕኖ ለአፍሪካ እድገት በምሁር የፓናል ውይይት ተደርጓሎ።

ዶ/ር ፍትህ እና ቤተሰቦቻቸው ለዚህ የበቁት በሲዳማ ክልል በሀዋሳ ለሰሯቸው ኤንቨስትመንቶች; ከፍተኛ የሆነ ማህበራዊ ጉዳይ (Corporate Responsibilies) እና በተለያዩ ወቅት ባገኟቸው የሀገር ውስጥ ስኬቶች፣ በአሁኑ ወቅት በከተማ በመስራት ላይ ያሉት በአፍሪካ በፋሲሊቲው በቀዳሚ ተርታ የሚቀመጥ የኢንተርናሽናል ሪዞርት እና ወተር ፓርክ እንዲሁም በሀገር አቀፍ እና በአህጉራዊ ባላቸው ሀላፊነቶች በሰሩት ስኬታማ ስራዎች እንደሆነ በመድረኩ ተገልጿል።

ዶ/ር ፍትህን ቤተሰቦቻቸውንና የስራ ባልደረቦቻቸውን እንኳን ደስ አላችሁ።

#CiBEL #centralyamarechhawassahotel #DrFeteh Weldesenbet #Abidjan

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጥምቀት በዓል በመላ ሀገሪቱ በድምቀት እየተከበረ ነው

የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እና በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት...

“ሎዛ ዘፀአት”እና “የሎዛ ድርሳናት”ተከታታይ ረጅም ልቦለድ መጻሕፍት ተመረቁ

በጋዜጠኛና ደራሲ መርዕድ እስጢፋኖስ የተጻፉት ሎዛ ዘፀአት(2014 ዓ.ም) እና...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል አደረሳችሁ፣ አደረሰን!! በክርስቲያኖች ዘንድ ጥምቀት...

የአርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ

የአርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ስርዓተ ቀብር በመንበረ ጸባኦት ቅድስት...