ጎግል የቀረበበትን ክስ ለማስቆም 68 ሚሊየን ዶላር ለመክፈል ተስማማ

Date:

ጎግል የድምፅ እገዛ መተግበሪያው ጎግል አሲስታንት የሰዎችን ንግግር ያደምጣል በሚል በካሊፎርንያ ፍርድ ቤት ቢከሰስም፣ አሁን 68 ሚሊየን ዶላር በመክፈል ክሱን ለማቋረጥ መስማማቱ ተነግሯል።

በክሱ መተግበሪያው ያለ ሰዎች ፈቃድ እንደሚሰራና የሰዎችን ንግግር እንደሚያደምጥ እና ንግግሮቹን ወደ ጎግል እንደሚልክ ተመላክቶ ነበር።

ጎግል ክሱን ለማቋረጥ 68 ሚሊየን ዶላር ለመክፈል መስማማቱን ሲገልፅ፣ የአሜሪካ ዳኛ ስምምነቱን እንዲያፀድቁት ግን ይጠበቃል ተብሏል።

በተመሳሳይ ከሳምንታት በፊት የአፕሉ ሲሪ ተመሳሳይ የሰዎችን ንግግር ያደምጣል የሚል ክስ ተከፍቶበት 95 ሚሊየን ዶላር በመክፈል ክሱን ለማቋረጥ መስማማቱ ይታወሳል።

መረጃው ከአናዶሉ የተገኘ ነው። tikvahethmagazine

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግብጻዊቷ የቴሌቪዥን አዘጋጅ በዕፅ ዝውውር ወንጀል የሞት ፍርድ ተወሰነባት

የካይሮ የወንጀል ችሎት፤ ዕውቋን የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ሳራ ካሊፋን...

ከአሜሪካ ጋር የሚኖረው “የጨዋታው ሕግ ተቀይሯል፤ የተመጣጠነ ምላሽ ዘመን አብቅቷል

ኢራን ከአሜሪካ በኩል ለሚሰነዘርባት ጥቃት የምትሰጠው ተመጣጣኝ የአጸፋ ምላሽ...

የ2.5 ቢሊየን ብር ግዙፍ ፕሮጀክት በአታ ለማርያም ገዳም በመስከረም ወር የመሠረት ድንጋይ ሊያኖር ነዉ

​በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ የታዕካ ነገሥት...

የዲቪ ዕድለኞች የማመልከቻ ሂደታቸውን እንዲቀጥሉ ተወሰነ!

የአሜሪካ የፌዴራል ፍርድ ቤት በዲቪ ሎተሪ አመልካቾች የማመልከቻ ሂደት...