ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቆይታቸው ከአገሪቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽ እና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ከዚህ ጉዟቸው ቀደም ብሎ ወደ ጅቡቲ በማቅናት የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ መሐሙድ እና የጅቡቲ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ኢስማኢል ዑመር ጌሌ በተገኙበት የሦስትዮሽ ውይይት አካሂደዋል።
በውይይታቸው ላይ መሪዎቹ በሦስቱ አገራት መካከል ያለውን ዘርፈ ብዙ ትብብር ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
ምክክር ከተገደረገባቸው ጉዳዮች አንዱ ሽብርተኝነትን በጋራ ለመዋጋትና በአፍሪካ ቀንድ አስተማማኝ ሰላም ማስፈን ነው።
የጋራ ኢንቨስትመንትን ማሳደግ፣ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን ማጠናከር እና የቀጣናውን የኢኮኖሚ ውህደት ለማፋጠን የመሠረተ ልማት ትስስርን ስለማሳደግ ሰፊ ውይይት መደረጉን ከሶማሊያ ፕሬዜዳንት ፅ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
