የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አርብ ከግብፅ ጋር ያለበትን የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ አስመልክቶ በዛሬው ዕለት መግለጫ ተሰጥቷል።
የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ባህሩ ጥላሁን “ ጨዋታው ልዩ ትኩረት የሰጠነው ነው “ ሲሉ ገልጸዋል።
“ ጨዋታው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን እንዲሁም የኢትዮጵያ ህዝብም ትልቅ ትርጉም የሚሰጠው ጨዋታ ነው “ ሲሉ አቶ ባህሩ ጥላሁን ተናግረዋል።
አክለውም “ ጨዋታው ትልቅ ታሪካዊ አሻራችንን ያስቀመጥንበት ህዳሴ ግድብ በሚመረቅበት እና ንጋት ሀይቅ በተሰየመበት ሰዓት ስለሆነ የሚደረገው ትልቅ ትኩረት ሰጥተነዋል “ ብለዋል።
“ ቡድኑ የተቻለውን ሁሉ እንዲያደርግ እንፈልጋለን ያንን እንዲያደርግም ነው ቀደም ብሎ ዝግጅት እንዲጀምር ያደረግነው “ አቶ ባህሩ ጥላሁን
የዋልያዎቹ ዋና አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ በበኩላቸው “ ጠንካራ ጨዋታ ነው የሚጠብቀን “ ብለዋል።
“ እኛም በዛው ልክ ተገቢውን ጥሩ ዝግጅት አድርገናል ሜዳ ላይ የሚሆነውን እናያለን “ ሲሉ አሰልጣኙ ተናግረዋል።
@tikvahethsport
