መምሪያው ለፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር በጻፈው ደብዳቤ ማኅበሩ ከተቋቋመበት ዓላማ ውጭ ርቱዕ እምነትን ከሥነ ምግባር ጋር ይዞ የሚኖረውን ሕዝበ ክርስቲያን ያሳዘነ፣ እናት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ለጠላት መሳለቂያ እንድትሆን ያደረገ ከቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ጋር የሚቃረን እመቤታችን ቤዛ አይደለችም የሚል ጤናማ ያልሆነ ትምህርት ሚያዝያ 10 ቀን 2017 ዓም በማኅበሩ ሚዲያ ማስተላለፉን እንደተመለከተ ገልጾ የማኀበራት ምዝገባ ክትትል እና ቁጥጥር መምሪያው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ጸድቆ በተሰጠው ደንብ መሠረት በማኅበራት መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ዙሪያ ጥያቄ የሚያስነሱ ጉዳዮች ሲፈጠሩ ተገቢውን ክትትልና አስፈላጊውን እርምት የመስጠት ሓላፊነት ያለበት በመሆኑ በደብዳቤው ለተጠቀሱ አምስት ነጥቦችን በማኅበሩ በኩል አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥባቸው በጥብቅ አሳስቧል።
መምሪያው በጻፈው ደብዳቤ ላይም በዕለተ ስቅለት የተላለፈው ትምህርት ቪዲዩ በአስቸኳይ ከማኅበሩ ዩቲዩብ እንዲወርድ እንዲያደርግና በዕለቱ የተላለፈውን ትምህርት ሙሉ ቪዲዮ ቅጂ ለመምሪያው እንዲያቀርብ ጥብቅ መመሪያ ሰጥቷል።
©ኢኦተቤ ሕዝብ ግንኙነት
#አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ
