ሀርቫድ ዩኒቨርሲቲ የትራምፕ አስተዳደርን ከሰሰ

Date:

የትራምፕ አስተዳደር በሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ዓለም አቀፍ ተማሪዎችን የመቀበል መብት ላይ ክልከላ ጥሎ ነበር።

የሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አለን ጋርበር የትራምፕ አስተዳደርን ውሳኔ በመቃወም ክስ መስርተዋል።

በዚህም መንግሥት የሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲን አንድ አራተኛ ተማሪዎች ለማስወገድ ሞክሯል፤ ዓለም አቀፍ ተማሪዎች ለዩኒቨርሲቲው ተልዕኮ ትልቅ ሚና አላቸው፤ ያለእነርሱ ሀርቫርድ ሀርቫርድን አይሆንም፤ ይህን ሕገ-ወጥ ውሳኔ እንቃወማለን ብለዋል።

የትራምፕ አስተዳደር ውሳኔውን ያሳለፈው የማስተማር ነጻነታችንን ለመጋፋት ያደረገውን ሙከራ ባለማስተናገዳችን ነው ያሉት አለን ጋርበር፤ መንግሥት የትምህርት አሰጣጡን፣ ተማሪዎቻችንን እና የትምህርት ክፍሎችን እንዲቆጣጠር አንፈቅድም ሲሉ ተናግረዋል።

ሀርቫርድ በካምብሪጅ ካምፓሱ ብቻ 6 ሺህ 800 ገደማ ከ100 በላይ አገራት የተውጣጡ የውጭ ተማሪዎችን የሚያስተናግድ ሲሆን፤ ከእነዚህም አብዛኛዎቹ የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ናቸው።

የትራምፕ አስተዳደር ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ በካምፓሱ ውስጥ ውዥንብር መፈጠሩን የገለፀው የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር፤ ዓለም አቀፍ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ለመቆየት ወይም ለመሰናበት በሁለት ውሳኔዎች መካከል እንደሚገኙ አክሏል።

የሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ያቀረበውን አቤቱታ ተከትሎ በቦስተን የሚገኘው ፍርድ ቤት የትራምፕ አስተዳደር ውሳኔ ለጊዜው ተፈፃሚ እንዳይሆን አግዷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...