አሌክስ አብርሃ
ቻይናዊው ለኢትዮጵያዊት ሚስቱ “አሪፍ ምሳ ስሪልኝ ” ብሎ ያመጣውን ጥቅል ነገር ያቀብላታል። የሚስት እናት በእንግድነት ሄደው ነበርና ያው እንደኢትዮጵያ አባወራ ስጋ በኪሎ ገዝቶ ይሆናል ብለው ቢከፍቱት …እንቁራሪት፣ ፌንጣ፣ በረሮ።
መቸስ የሰው አገር ሰው ብለው አፍንጫቸውን ይዘው ሲሰራም ሲበላም አዮ…እና ቻይናዊው የተረፈውን ምግብ እየጠቆመ “በደንብ ከድነሽ አስቀምጭልኝ” ይላል። እናት ተበሳጭተው ምናሉ ?
“ኡኡቴ! ምን እንዳይገባበት?”
ቤን ሂን የፃፋቸውን መፅሐፎቹን ከሞላ ጎደል አንብቢያቸዋለሁ። በተለይ የቲዮሎጅ መፅሐፍቶቹን። ስብከቶቹንም ቢሆን የሚበዙትን ሰምቻለሁ፤ ነገሩ ንፅፅር ነውና ከእኛ አገር በርካታ ፓስተሮችና መጋቢወች ነብያትና “ሐዋርያት” ስሁት አስተምሮ አንፃር ሰውየውን አበላሽተን እንዳንልከው ነው ፍርሃቴ። ሁሉንም ስህተት ተሳስተን ጨርሰናል።
የሰማይ አምላክ ራሱ ለህዝቡ ሲል ተዓምር ካልፈጠረ ኢትዮጵያዊያን ካለን ስህተት፣ ሰይጣን የሚደነቅበት የተጨማለቀና መረን የለቀቀ መንፈሳዊ አስተምሮና መንፈሳዊ ልምምድ በላይ የውጭ አገር ሰው ገብቶ እንዳይበክለን “እንክደነው” ግርግር ቀልድ ነው! ምን እንዳይገባ? በአካል እንዳይገባ በር ስለዘጋን ልናቆመው? አስተምሮቱ እንደሆነ ኢንተርኔቱን አጥለቅልቆታል።
ሰውየው ላይ ሳይሆን አስተምሮቱን ሞግቱ። አስራ ምናምን የአፍሪካ አገራት ይዞራልና ለአፍሪካዊያን ወንድሞቻችሁም ትተርፉ ይሆናል!
ስህተት ነው፣ ልክ ነው የሚለው ይቆየንና ከሰውየው አንድ ነገር መውሰድ እንችላለን! ይሄ በየመንደሩ እንደአሸን የፈላ ባለማይክና ባለሱፍ ፣ እንጥሉ እስኪወርድ የሚዘልና የሚጮህ ((((በጥልቀት ማንበብን)))) ከቤን ሂን ቢማርና ቢሞግት ይሻላል። መበሳጨት አይጠበቅባችሁም፤ መፅሐፍቱን እየጠቀሳችሁ አስተምሮቱ ላይ መነጋገር ከፈለጋችሁ ያው ሜዳው ለመማር ዝግጁ ነን
