ለታላቁ የሕዳሴ ግድብ የመልካም ምኞት መላኪያ ቁጥር

Date:

ሁሉም ኢትዮጵያውያን በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ድል የተሰማቸውን ደስታ ማጋራት የሚችሉበት የመልካም ምኞት መላኪያ ቁጥር ይፋ ሆኗል፡፡

ማንኛውም ሰው የእጅ ስልኩን በመጠቀም ወደ 8120 የመልካም ምኞት መልዕክቱን ከዛሬ ጀምሮ መላክ እንደሚችል ተገልጿል፡፡

የአጭር ፅሑፍ መላኪያ ቁጥሩን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ይፋ አድርገውታል።

መርሐ ግብሩ ከዛሬ ጀምሮ እስከ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚቆይ ተገልጿል።

ዜጎች ዲጂታል አሻራን በመጠቀም የድል ብስራት መልዕክታቸውን በ8120 በሚልኩበት ወቅት:-

1 ቁጥር “በህብረት ችለናል” መልዕክት በመጫን = 5 ብር ድጋፍ

2 ቁጥር “ህዳሴ ግድብ የብልጽግናችን አሻራ” መልዕክት በመጫን = 10 ብር ድጋፍ

3 ቁጥር “ግድባችን የአሸናፊነት ድል አክሊል” መልዕክት በመጫን = 15 ብር ድጋፍ

4 ቁጥር “ግድባችን የዓባይ ዘመን ትውልድ የተጋድሎ ሰንደቅ” መልዕክት በመጫን 100 ብር ድጋፍ ወይም የራስን መልዕክት ሲልኩ 20 ብር ድጋፍ ማድረግ እንደሚቻል ተገልጿል።

እነዚህን  አማራጮች በመጠቀመ  የድል ብስራቱን መልዕክት ለታሪክ ማኖር እንደሚገባም ጥሪ ቀርቧል።

በዕለቱ ኢትዮ ቴሌኮም ለግድቡ እውን መሆን ላበረከተው አስተዋፅኦ ከታላቁ የሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ምስጋና ቀርቦለታል።

በሥነ- ሥርዓቱ ላይ የተላቁ የህዳሴ ግድብ የምክር ቤት አባላትን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት በዛሬ ዕትሟ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ነሔሴ 16 2018 ዓ.ም ገበያ...

ቱርክ ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ አወጣች

ቱርክ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ ዓለም አቀፍ...

በመቀለ የሚካሄደው የአሸንዳ በዓል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተሰረዘ

በትግራይ በርካታ ታዳሚ በሚገኝበት በየዓመቱ የሚከበረው የአሸንዳ ባህላዊ በዓል...

የኢትዮጵያ ፖስታ 3 ሺሕ የሚጠጉ ቅርንጫፎቹን ወደ ባንክ ኤጀንትነት ለመቀየር እንቅስቃሴ ጀመረ

የኢትዮጵያ ፖስታ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ 3 ሺሕ በሚጠጉ ቅርንጫፎቹ...