ማቲያስ ተፈራ በአዲስ አልበም ሊመጣ ነው

Date:

ከ ሀያ አንድ(21) አመት በኃላ ተወዳጁ የዘጠናዎቹ ድምፃዊ ማቲያስ ተፈራ በአዲስ አልበም በቅርቡ ብቅ እንደሚል ገልጿል፡፡ ድምፃዊ ማቲያስ በይበልጥ በህዝብ ዘንድ የሚታወቅበት “ልብሽማ እንደው ልብሽማ ”  በተሰኘው ሙዚቃ ነው፡፡

ከ ሀያ አንድ(21) ዓመት በኃላ አዲስ አልበሙን ሊያደርሰን እየተዘጋጀ  ይገኛል፡፡ በአዲሱ ሙዚቃ በርካታ ከያኒያን ሲሳተፉ ነፍሳቸውን ይማር  ተወዳጆቹ ድምፃዊ ታምራት ደስታ ሁለት(2) ግጥሞቾ እና ዜማ ደርሶ በመስጠት እንዲሁም የድምፃዊ ብስራት ሱራፌል አባት የሆነው ተወዳጁ የግጥም ዜማ ደራሲ ድምፃዊ ሱራፌል አበበ እንደ ተሳተፈ ተገልጿል፡፡

በዜማ በኩል ደግሞ ተወዳጁ አለማየሁ ደመቀ ፣ ሳሚ ሎሬት ፣ አማኑኤል ይልማ ፣ ታመነ
መኮንን ፣ሚካኤል ሀይሉ (ሚኪ ጃኖ)  በግጥሙ አብታሙ ቦጋለን ጨምሮ ተሳትፈዋል፡፡

በቅንብሩ አበጋዝ ክብረ ወርቅ ፣ ካሙዙ ካሳ ፣ሚካኤል ሀይሉ (ሚኪ ጃኖ)፣ ክብረት ዘኪዎስ ስቱዲዮ (ኤክስፕረስ ባንድ)፡፡

በሙዚቃ መሳርያ ያጀቡት ዘሪሁን በለጠ በሳክስፎን፣ ቤዝ ጊታር አንጋፋው ድምፃዊ ዳዊት ፅጌ ፣ ክብረት ዘኪዎስ(ኤክስፕረስ ባንድ) ሊድ ጊታር ተሳትፈዋል በጨማሪ የድምፁን ሪከርድ ክብረት ዘኪዎስ ስቱዲዮ ተጠናቋል፡፡

ፋውቸር (አብሮ በመዝፈን) የተሳተፉት አጋቱ የተባለ ድምፃዊ ሁለት ዘፈኖች ያህል እንደ ተሳተፉ ድምፃዊው ገልጿል ፡፡በነገራችን ላይ “ልብሽማ” የተሰኘ ስራ ዜማውን የሰራው የ ብስራት ሱራፌል አባት ሱራፌል አበበ እንደ ሆነ ይታወቃል፡፡ለዘመናት የማይፋቅ አሻራ ለድምፃዊ ማትያስ ተፈራ እንደሰጠው አይካድም ፡፡

በቅርቡም አዲስ አልበም እንደ ሚለቀቅ ቀልፆ ከዛ በፊት የአልበም መዳረሻ ይሆን ዘንድ በፊት ከሰራቸው ሶስት ሙዚቃዎች እንዲሁም ሶስት አዳዲስ የሙዚቃ ስራ በራሱ ዩትዮብ ቻናል ይለቃል፡፡ ዩትዮብ ቻናሉን ተቀላቀሉ https://youtube.com/@matiyasteffera1780?si=s-fa40DcfXuq-mif

via ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የምርጫ ካርድ፡ የአገር ባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ

ግዮን መጽሔት :- በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ጉዞ ውስጥ ምርጫዎች የሥልጣን...

አደይ ኢትዮጵያ ጓል አስመራ…!!

የቀድሞ ፕ/ት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የስንብት ቃል ለጠቅላይ ሚ/ር ዐብይ...

ትራምፕ ከኢራን ጋር በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ሁለተኛው ዙር ድርድር ሊደረግ እንደሚችል ተናገሩ

ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚደረገው ሁለተኛ ዙር የሰላም ድርድር...

በ”ፊንቴክ” ኢንቨስትመንት በተጠረጠሩት ላይ ተጨማሪ ጊዜ ተፈቀደለት

ፖሊስ ተጨማሪ 14 ቀን ለምርመራ እንዲፈቀድለት ባለፈው አርብ በነበረው...