ሜታ ከግማሽ ቢሊዮን ዶላር በላይ ተቀጣ

Date:

ሜታ የተሰኘው ማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያ ህጻናትን ከኦንላይን አደጋዎች መጠበቅ አልቻለም እና «በሕዝብ ላይ ስጋት» ሆኗል በሚል በኒው ሜክሲኮ ግዛት ፍርድ ቤት ከግማሽ ቢሊዮን ዶላር በላይ (በአጠቃላይ 567 ሚሊዮን ዶላር) የገንዘብ ቅጣት ተላለፈበት።

የኒው ሜክሲኮ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ራኦል ቶሬዝ በጎርጎርሳዊው 2023 ባቀረቡት ክስ፤ የሜታ አልጎሪዝም አዋቂዎችን ወደ ታዳጊዎች ይዘቶች እንዲመሩ እንደሚያደርግ እና ኩባንያው በወጣቶች ላይ ስላለው አደጋ በውስጥ ጥናት ያወቃቸውን መረጃዎች ደብቋል የሚል የተጠቃለለ ክስ መቅረቡ ታውቋል።

ከተላለፈው አጠቃላይ የገንዘብ ቅጣት ውስጥ ሦስት አራተኛው በአምስት ዓመታት ውስጥ ተከፍሎ ለአእምሮ ጤና ህክምና የሚውል ሲሆን፤ ቀሪው ገንዘብ ደግሞ ለግንዛቤ ማስጨበጫ እና መከላከያ መርሃግብሮች ይከፋፈላል ተብሏል።

ሜታ በውሳኔው እንደማይስማማና ይግባኝ እንደሚል ቢገልጽም፣ ፍርድ ቤቱ ግን ህጻናትን ለጥቃት በመዳረጉ ጥፋተኛ ሆኖ ማግኘቱን አስታውቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የታሰሩ የፖለቲካ ታጋዮች እንዲፈቱ ተጠየቀ

ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት መንግሥት በጠባብ ቀዳዳ የምታየውን የፖለቲካ ምኅዳር...