ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በብራዚል-አፍሪካ ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ ነው

Date:

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የተመራ ልዑክ በ2ኛው የብራዚል-አፍሪካ የምግብ ዋስትና ረሃብን መከላከል እና የገጠር ልማት ጉባዔ ላይ እየተሳተፈ ነው፡፡

በብራዚል ዋና ከተማ ብራዚሊያ ዛሬ የተጀመረው ጉባዔው ‎በብራዚልና በአፍሪካ ሀገራት መካከል በግብርና በምግብ ዋስትና በንግድና በዘላቂ ልማት ዘርፎች ላይ ተጨባጭ እድገት ለማምጣትና ትብብርን ለማጎልበት የተዘጋጀ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ጉባዔው ‌‎ለግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ ሰፊ ፋይዳ እንዳለውም ነው የተገለጸው፡፡

‎በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራው ልዑክ ከጉባዔው ጎን ለጎን ከብራዚል ምክትል ፕሬዚዳንት እንዲሁም የኢንዱስትሪና ልማት ሚኒስትር ጀራልድ ሮድርጌዝ አልካሚን ጋር ተወያይቷል።

‎አቶ ተመስገን በዚሁ ወቅት፥ የባለብዙ ወገን ትብብርንና ሌሎች ፈጣን ለውጥ የሚያመጡ አሠራሮችን ለመተግበር በጋራ አቅጣጫ ማስቀመጣቸውን ተናግረዋል።

‎ምክትል ፕሬዚዳንቱ በበኩላቸው፥ የኢትዮጵያን ፈጣን እድገትና በጥሩ መሰረት ላይ የሚገኘውን የሀገር ውስጥ ምርት መነቃቃትን አድንቀዋል፡፡

ሀገራቸው በተለይም ኢትዮጵያ በምትታወቅበት ጠንካራና ዘመናዊ የአቪዬሽን ዘርፍ በጋራ የመሥራት ፍላጎት እንዳላትም አረጋግጠዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...