የድምጻዊት ሐይማኖት ግርማ “ጅንኑ”የተሰኘው አራተኛ አልበም  ለአድማጭ ሊቀርብ ነው

Date:

ከዚህ በፊት ሶስት አልበሞች ለአድማጭ ያቀረበችው ኦማሔሬ በተሰኘው የሙዚቃ ስራ ከአድማጮቿ ጋር የተዋወቀችው ሐይማኖት ግርማ አራተኛ አልበሟ ለህዝብ ልታደርስ ቀን ቆርጣለች።

አዲሱ አራተኛ አልበሟ 12 ያህል ትራኮች እንደያዘ የተናገረችው ድምጻዊቷ በርካታ የሙዚቃ ሰዎች እንደተሳተፉበት ተናግራለች።

ድምጻዊቷ ሙዚቃ በግል ጉዳይ ምክንያት ላለፉት 12 አመታት አቁማ የነበረ ቢሆንም በጓደኞቿ ምክንያት ዳግም ወደ ሙዚቃው አለም በመምጣት አራተኛ አልበሟ ለመስራት በቅታለች።

ታምሩ አማረ ሚኪ ጃኖና ሌሎችም ስመጥር የሙዚቃው ሰዎች ተሳትፈውበታል ተብሏል።

አልበሙን ሰርቶ ለመጨረስ አንድ አመት ብቻ እንደወሰደባት የተናገረችው ሐይማኖት ግርማ በወጪም በኩል የተጋነነ ዋጋ አልተጠየኩበትም ብላለች።

አዲሱ አልበም ከበፊቶቹ አልበም እኩል እንዲደመጥ ጥራቱን ጠብቆ ተሰርቷል ነው የተባለው።

ሙዚቃውን ፕሮዲውስ ያደረገው ድምጻዊ ደሜ ሉላ አዲሱ የሐይማኖት ግርማ አልበም በናሆም ሪከርድስ በኩል ለአድማጭ ይቀርባል ብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ በጡረታ ከኃላፊነታቸው ተሰናበቱ

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያንና የአዲስ አበባ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ...

አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ አዲስ መግለጫ አወጣች

ታዋቂዋ አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ ለስፖርት ወዳጆችና ለደጋፊዎቿ ወቅታዊ መረጃ...

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...