ሞርጌጅ ባንክ ወይም የቤት ብድር ባንክን ሀላፊነት ወስዶ መልሶ እንዲደራጅ ጥያቄ ቀረበ

Date:

በሀገሪቱ ቀድሞ የነበረዉ የሞርጌጅ ባንክ ባልታወቀ ምክንያት ወደ ንግድ ባንክ መቀላቀሉም ተገልፆል።

ይህ የተጠየቀዉ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴርን የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በገመገመበት ወቅት ነው።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ፣ መሠረተ-ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ፕ/ር መሃመድ አብዶ በግምገማዉ ወቅት መንግስት በቤቶች ልማት ላይ ያለውን የፋይናንስ ችግር ለመፍታት የሞርጌጅ ባንክ መልሶ ማደራጀት አለበት ሲሉ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ቀደም ባሉት ዘመናት የቤት ብድር ባንክ ሞርጌጅ እንደነበረና ባልታወቀ ምክንያት ወደ ንግድ ባንክ የተቀላቀለ መሆኑን የቋሚ ኮሚቴዉ ምክትል ሰብሳቢ ዶ/ር እሸቱ ተመስገን ተናግረዋል።

የዜጎችን የቤት ችግር ለማቃለል የታቀደውን የቤቶች ልማት ለማከናወን አንዱ ተግዳሮት በቤት ልማት ላይ ያለው የፋይናንስ አቅርቦት ውስንነት መሆኑን በግምገማው ወቅት ተገልፆል።

የቋሚ ኮማቴዉ ሰብሳቢ ኘ/ር መሀመድ የቤት ችግርን ሙሉ በሙሉ መፍታት ባይቻልም በሌሎች ሀገራትም ችግሩን ለመፍታት ከሚጠቀሙባቸው ዘዴዎች አንዱ የቤት ብድር ባንክ አገልግሎት መሆኑን ጠቅሰዋል።

ስለሆነም መንግስት አዲስ ከማዋቀር ይልቅ የነበረውን የኮንስትራክሽን ባንክ መልሶ ማደራጀት እንዳለበት አሳስበዋል።

የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ኃላፊነቱን ወስዶ ይህንን ባንክ መልሶ እንዲደራጅ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል
‎
‎አያይዘውም ዜጎች ተደራጅተው በረጅም ጊዜ ክፍያ የቤት ባለቤት ሊሆኑ የሚችሉበት የባንክ አገልግሎት በመሆኑ ስርአቱ መዘርጋት እንዳለበት አክለዋል።

የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሣኒ የሞርጌጅ ስርዓት እንዲዘረጋ የምክር ቤቱና የቋሚ ኮሚቴው ክትትልና ድጋፍ ያስፈልጋል ብለዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ10 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ጥቅምት 12 ቀን 2019...

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ የፕላቲንየም ብራንድ የማስተር ካርድ ይፋ አደረጉ

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ደንበኞች የፕሪሚየም...

የአሜሪካ የደህንነት ኃላፊ ኢራንን አስጠነቀቁ

ቡሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተር ጄይ ክላይተን አርብ ዕለት ኢራን በውጭ...

ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ  በአመት ከ1.1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ታጣለች

85 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በግብርናው ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን...