ሲፒጄ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት የአዲስ ስታንዳርድን ምዝገባ በአስቸኳይ እንዲመልሱ አሳሰበ

Date:

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የአዲስ ስታንዳርድን የበየነ መረብ ሚዲያ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ከየካቲት 17 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ መሰረዙን ተከትሎ፣ የዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (CPJ) የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት የገለልተኛውን ተቋም ምዝገባ በአስቸኳይ እንዲመልሱ ጥሪ አቀረበ።

የሲፒጄ የአፍሪካ ዳይሬክተር አንጄላ ኩዊንታል “ይህ ቁጥጥር ሳይሆን በቀል ነው፤” ሲሉ ተናግረዋል። አክለውም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን “ብሔራዊ ጥቅም” እና “የሚዲያ ሥነ-ምግባር” የሚሉ ግልጽ ያልሆኑ መመሪያዎችን እንደ መሣሪያ በመጠቀም ገለልተኛ ጋዜጠኝነትን እያፈነ ይገኛል ብለዋል።

“የአዲስ ስታንዳርድን የሥራ ፈቃድ መሰረዝ በኢትዮጵያ ውስጥ ወሳኝ የሆኑ ዘገባዎችን ለማዳከም የታቀደ የተቀናጀ ዘመቻ አካል ነው” ሲሉ ገልፀው “ባለሥልጣናት የተቋሙን ምዝገባ በአስቸኳይ ሊመልሱና በፕሬስ ላይ እያደረሱት ያለውን እየተባባሰ የመጣ ጥቃት ሊያቆሙ ይገባል” ብለዋል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ትናንት የካቲት 17 ቀን 2018 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፤ አዲስ ስታንዳርድ “የሚዲያ ሥነ-ምግባርን የሚጥሱ፣ የኢትዮጵያን ሕግ የሚቃረኑ እንዲሁም የሀገርንና የሕዝብን ብሔራዊ ጥቅም አደጋ ላይ የሚጥሉ ዘገባዎችን በተደጋጋሚ ሲያሰራጭ ቆይቷል” ሲል ከሷል።

ባለሥልጣኑ አክሎም፣ “ለተቋሙ በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ቢሰጠውም የሚዲያ ተቋሙ የማስተካከያ እርምጃ ሳይወስድ በመቅረቱ፣ በኢትዮጵያ የሚዲያ አዋጅ መሠረት ምዝገባው እንዲሰረዝ መደረጉን ገልጿል”።

የአዲስ ስታንዳርድ ዋና አዘጋጅ ዮናስ ከድር በበኩላቸው ውሳኔውን ውድቅ ያደረጉ ሲሆን፣ ተቋሙ ከመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ምንም ዓይነት ይፋዊ ማሳሰቢያ ደርሶት እንደማያውቅ ገልጸዋል። “ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያዎች ተሰጥተዋል” የሚለው አባባል ከእውነት የራቀ መሆኑን በመጥቀስ፣ ተቋሙ ሕጋዊ የፍትሕ ሂደቱን ለማረጋገጥ አማራጮችን እየመረመረ መሆኑን አስታውቀዋል።

ይህ እርምጃ በቅርቡ በሚዲያዎች ላይ የተወሰደን ተከታታይ እርምጃ ተከትሎ የመጣ ነው፡፡

ለአብነትም በቅርቡ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን #ዋዜማ ሬዲዮ በኢትዮጵያ ያለውን የስራ ፈቃድ እንዲመልስ መደረጉን ማስታወቁ የሚታወስ ነው፡፡በወቅቱ “እርምጃው በማንኛውም መመዘኛ ትክክል ነው ብለን አናምንም”፤ “አሳዝኖናልም” ሲል ጣቢያው ባወጣው መግለጫ መግለጹ አይዘነጋም።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ መንግሥት የካቲት 6/2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚገኙ ሦስት የ #ሮይተርስ ጋዜጠኞችን የሥራ ፈቃድ ለማደስ ፈቃደኛ ሳይሆን መቅረቱን የዜና ወኪሉ መግለፁ ይታወሳል።

በተጨማሪም የጀርመኑ ዜና ወኪል #ዶይቸ_ቬለ (DW) የሚሰሩ ሁለት የአገር ውስጥ ጋዜጠኞች የስራ ፈቃዳቸው በዘላቂነት መታገዱ የሚታሰው ሲሆን፤ የቢቢሲ ዘጋቢዎችም የሥራ ፈቃዳቸው ሳይታደስ መቅረቱ የኢትዮጵያን የሚዲያ ምህዳር ይበልጥ አሳሳቢ አድርጎታል ተብሏል።

አዲስ ስታንዳርድ ራሱ በተደጋጋሚ የመንግሥት እርምጃዎች ሰለባ ሆኗል። ለአብነትም በሚያዝያ ወር 2017 ዓ.ም ፖሊስ የተቋሙን የአንድ ባልደረባ መኖሪያ ቤት በመበርበር፣ ሦስት ሥራ አስኪያጆችን በቁጥጥር ስር በማዋል ንብረቶቹን ወስዶ ነበር። ቀደም ሲልም በሰኔ ወር 2013 ዓ.ም. የአሳታሚው የሥራ ፈቃድ በመነጠቁ ተቋሙ ታግዶ እንደነበር ይታወሳል።

እ.ኤ.አ. በ2011 የተመሠረተው አዲስ ስታንዳርድ፣ በወሳኝ የፖለቲካ ዘገባዎቹ የሚታወቅ ሲሆን፣ አሁን የተላለፈበት የፈቃድ ስረዛ ውሳኔ በኢትዮጵያ ውስጥ በሕጋዊ መንገድ እንዳይንቀሳቀስ ያግደዋል።

ሲፒጄ አስተያየት እንዲሰጠው ለኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በኢሜይል ላቀረበው ጥያቄ፣ እስካሁን ድረስ ምንም ዓይነት ምላሽ አላገኘም።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጥቃት አድራሹ ከካሊፎርኒያ መሆኑን ትራፕ ገለፁ

ትናንት ቅዳሜ ምሽት በዋይት ሃውስ የጋዜጠኞች ማኅበር የእራት ግብዣ...

በኬንያ የመንገደኞች አውሮፕላን ከመስመሩ ወጥቶ ተከሰከሰ

ዛሬ ረፋድ ላይ በኬንያ ማንዴራ የአውሮፕላን ማረፊያ አንድ...

አቶ ጀማል አህመድ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨማሪ 26 ሚሊየን ብር ሰጡ

አቶ ጀማል አህመድ ባሳለፍነው ወር ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ  ከሰጠው...

“የቻይና-አፍሪካ የምርምር ማዕከል”በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሊከፈት ነው

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከቻይና-አፍሪካ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር "የቻይና-አፍሪካ የምርምር...