ሴኔጋል ተአምር ሰራች

Date:

ከዳካር በስተደቡብ ምስራቅ 32 ኪ.ሜ ርቀት ላይ እጅግ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ከተማ እየገነባች የምትገኘው ሴኔጋል በ1ቢሊዮን ዩሮ ያስገነባችዉን 14 ጣቢያዎችን ያሉት ዋና ከተማዋን ዳካርን ከዲያምኒያዲዮ ጋር የሚያገናኘውን የዳካር ሪጅን ኤክስፕረስ ባቡር ጣቢያ አስመረቀች።

ይህ በቀን ወደ 115,000 የሚጠጉ መንገደኞችን አገልግሎት መስጠት የሚችል ጣቢያ በ45 ደቂቃ ውስጥ ዋና ከተማዋን ዳካርን ከብሌዝ ዲያግ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ (AIBD) ጋር የሚያገናኘው እጅግ ዘመናዊ የባቡር የትራንስፖርት ስርዓት ከ በ14 ጣቢያዎች እንዳሉትም ተነግሯል ።

በምዕራብ አፍሪካ ፈጣን ኢኮኖሚ ለዉጥ እያስመዘገበች የምትገኘው ሴኔጋል በዲሴምበር 2021 የጀመረው ይህ ፕሮጀክት በ 10 ደቂቃዎች ብቻ ባቡሩ የዳካርን ዋና ጣቢያ በሰዓቱ ለቆ ወደ ምስራቅ በማቅናት በአትላንቲክ ውቅያኖስ ዳርቻ ላይ በመዝለቅ በአንድ ወቅት ወሳኝ የወደብ ከተማ የሆነችውን ወደ ሩፊስክ ማገናኘት እንደሚችል የተነገረ ሲሆን ለ 40 ሽህ ሴኔጋላዉያን የስራ እድልን እንደፈጠረና ሀገሪቱን ከጫፍ እስከጫፍ ማገናኘት መቻሉ ነዉ የተገለጸው ።

ሀገሪቱ አዲስ ዘመናዊ የእግር ኳስ ስታዲየም፣ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ፣ በርካታ የንፋስ እና የፀሀይ ኤሌክትሪክ ማመንጫዎች ለ 8 ሚሊዮን ወጣቶች የስራ እድል የሚፈጥሩ ፕሮጀክቶች እየሰራችና በዳካር እና በዲያምኒያዲዮ መካከል የኬብል መኪና ትራንስፖርት ፕሮጀክቶችን እየገነባች እንደሆነ የገለፀው አፍሪካ ቢዝነስ ነዉ ።

jezeera

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...