ሸበሌ ባንክ የ65.6 በመቶ የትርፍ ዕድገት ማስመዝገቡን አስታወቀ

Date:

ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሚሰጠው ሸበሌ ባንክ፣ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የ20.95 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን ገለጸ። ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ65.60 በመቶ ዕድገት የታየበት መሆኑ ተመልክቷል።

ባንኩ ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የቀረበው ሪፖርት እንደሚያሳየው፣ በበጀት ዓመቱ 570.3 ሚሊዮን ብር ጠቅላላ ገቢ ማግኘት የቻለ ሲሆን፣ ወጪውን ደግሞ በ544.06 ሚሊዮን ብር በመገደብ ውጤታማ የፋይናንስ ሥነ-ሥርዓት ማሳየቱ ተገልጿል።

የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ኢብራሂም ኡስማን ለባለአክሲዮኖች እንደገለጹት፣ የባንኩ የሀብት መጠን በ60.52 በመቶ በማደግ ከነበረበት 3.76 ቢሊዮን ብር ወደ 6.03 ቢሊዮን ብር ከፍ ብሏል። ይህም ባንኩ ካለፈው ዓመት በ2.28 ቢሊዮን ብር የሚበልጥ ተጨማሪ ሀብት ማፍራቱን ያሳያል ተብሏል።

ሸበሌ ባንክ በበጀት ዓመቱ 878.4 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ አክሲዮኖችን በመሸጥ የዕቅዱን 88 በመቶ ማሳካቱን በሪፖርተቱ ገልጿል። በዚህም የባንኩ ጠቅላላ ካፒታል 2.26 ቢሊዮን ብር መድረሱንና ለዚህ ስኬት የክልል መንግሥታት በአክሲዮን ግዢና በስትራቴጂካዊ አጋርነት እያደረጉት ያለው ተሳትፎ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ተጠቅሷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ10 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ጥቅምት 12 ቀን 2019...

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ የፕላቲንየም ብራንድ የማስተር ካርድ ይፋ አደረጉ

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ደንበኞች የፕሪሚየም...

የአሜሪካ የደህንነት ኃላፊ ኢራንን አስጠነቀቁ

ቡሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተር ጄይ ክላይተን አርብ ዕለት ኢራን በውጭ...

ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ  በአመት ከ1.1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ታጣለች

85 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በግብርናው ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን...